ክንዳቹ አይላላ
Kindachu Aylala
ሳሙኤል ተስፋሚካኤል · መልህቄ · 2022
Kindachu Aylala is an Amharic mezmur (worship song) by Samuel Tesfamichael, from the album Melihke (2022).
ክንዳችሁ አይላላ ጉልበታችሁ አይበላ የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ የናዝሬቱ እየሱስ አለ ከእኛ ጋራ ከግብፅ ከባርነት ከፈርዖን ብዛት ህዝቡን ያሳረፈ ከጭንቀት ከፍርሃት በእሳት በደመና በቀን ሌት የመራ ያው የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ መንገዱ እጅግ እሩቅ ቢመስል ሚከብድ ማያልቅ የአለም ኑሮ ፈተና ቢሆንም ትንቅንቅ ከእኛ ጋራ ያለው አለምን አሸንፏል እስከ ፅዮን ድረስ በድል ይመራናል ክንዳችሁ አይላላ ጉልበታችሁ አይበላ የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ አማኑኤል እርሱ አለ ከእኛ ጋራ ከእግዚአብሔር ጋር ሆነው የወጡ ወደ ሰልፉ የአንበሶችን አፍ ዘጉ የእሳትን ሃይል አጠፉ በቅንም ፈረዱ መንግስታቱን ድል ነሱ አለምን ኮነኑ ጣኦትን አፈረሱ ዛሬም ከበውናል እነርሱ እንደደመና ክንዳችን እንዳይላላ ጉልበታችን ይፅና የፃድቅ ጉልበቱ ነውና እምነቱ ቅዱሳን ካህናቱ እልፍ በሉ በርቱ ክንዳችሁ አይላላ ጉልበታችሁ አይበላ የእስራኤል አምላክ አለ ከእኛ ጋራ ተስፋውን የሰጠው አለ ከእኛ ጋራ ሃይልን በሚሰጠን ሁሉን እንችላለን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን ክንዳችን ይበርታ ጉልበታችን ይፅና አምላካችን ብርቱ ሁሉን ቻይ ነውና


