Gubae

ኢየሱስ ድል ነሳ

Eyesus Dil Nesa

ሳሙኤል ተስፋሚካኤል · መልህቄ · 2022

Eyesus Dil Nesa is an Amharic mezmur (worship song) by Samuel Tesfamichael, from the album Melihke (2022).

የጌቶች ጌታ ነው እየሱስ የማመልከው መፅሃፉን ወስዶ ማህተሙን የፈታ የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ ገናናው ኢየሱስ ብቻውን ድል ነሳ ከእርሱ ጋራ ሊሰለፉ የወደዱ ሁሉ አለፉ ኢየሱስ ግን አለ በዙፋኑ በማእረጉ በስልጣኑ የለም የለም እንደርሱ ያለ የለም በሰማይ የለም በምድር የለም/2 የከፈተውን ማን ይዘጋዋል የዘጋውን ማን ይከፍተዋል ተውባይ ከልካይ አንድ እንኩዋን የሌለው ቁልፉ እሱ እጅ ብቻ ነው ከዘላለም እስከ ዘላለም ህያው ሆኖ የሚኖር እንደርሱ የለም ከነገድ ከቁዋንቁ ህዝቡን የዋጀው የታርደው በግ እርሱ ብቻ ነው

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Samuel Tesfamichael

See all 55 songs by Samuel Tesfamichael