Gubae

የምሥራች

Yemeserach

አስራት ሙላቸው · ሕይወትህ ሕይወቴ · 2017

Yemeserach is an Amharic mezmur (worship song) by Asrat Mulachew, from the album Hiwoteh Hiwotie (2017).

መርገም ተሰበረ ቀንበር ተወገደ የምስራች ሆነ ፍርድም ተቀየረ አበሳችን ቀረ አህዛብም ዳነ በዳዊት ከተማ መድሃኒት የሆነ ጌታ ተወለደ ተጨንቃ ላለችው ለተቸገረችው ከሰማይ ወረደ ለዚህ ነው ደስ ያለን /2/ ከሰማይ የሆነ አዳኝ ስላገኘን ዛሬ የምስራች ተሰማ ዛሬ በዳዊተ ከተማ ዛሬ ከዕለታት ባንዱ ቀን ዛሬ (ሰማን መልካም ወሬ) መድሃኒት ክርስቶስ መጣ ጌታ ለህዝብ ሁሉ ሆነ ታላቅ ደስታ ነፍሱ ብርሃን ሳታይ በሰይጣን እስራት ነፃነትን ላጣ ተስፋ ቆርጦ ያለን የሚቅበዘበዝን አርነት ሚያወጣ በቤተልሄም ከታላላቆች ዘንድ ስፍራ ሳይታጣ ንጉስ ቤት ሲጠበቅ ሁሉን ሊያድን ወዶ ጌታ ከታች መጣ ለዚህ ነው ደስ ያለን /2/ ከሰማይ የሆነ አዳኝ ስላገኘን በጨለማ ሀገር በሞት ጥላ ሳለን ብርሃንህ በራ ህፃን ተወለደ ደህንነት ሚያመጣ የእግዚአብሄር ስራ ዘመኑ ደረሰ ድንግልም ፀነሰች ወንድ ልጅ ወለደች ድንቅ መካር ሃያል አምላክ ስላገኘች ምድር እልል አለች ለዚህ ነው ደስ ያለን /2/ ከሰማይ የሆነ አዳኝ ስላገኘን ስሙ ነው ድንቅ መካር / ሃያል አምላክ / የዘላለም አባት / የሰላም ዓለቃ / ስሙ ነው እረኞች ድምፅ ሰሙ መንጋ ሲጠብቁ ያደሩ በሜዳ በደስታ ዘለሉ የምስራች ሰምተው ድንግሊቱ ወልዳ ሊቃውንት ወደዱ ሊሰግዱለት መጡ በብዙ እልልታ ክብር በአርያም ለእግዚአብሄር ሆነ ለሰው ልጆች ደስታ ለዚህ ነው ደስ ያለን /2/ ከሰማይ የሆነ አዳኝ ስላገኘን

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Asrat Mulachew

See all 13 songs by Asrat Mulachew