Gubae

ክበርልኝ

Keberelegn

አስራት ሙላቸው · ሕይወትህ ሕይወቴ · 2017

Keberelegn is an Amharic mezmur (worship song) by Asrat Mulachew, from the album Hiwoteh Hiwotie (2017).

ቢልቃጡ ተሰብሮ ሽቶው ያውድህ ነፍሴም ትገዛልህ እምባዬም ይፍሰስ እኔ ዝቅ ልበል አንተን ከፍ ላርግህ ክብሬን ልጣልና ክብርህን ላምጣልህ ክበርልኝ /8/ ያጢያተኛው ወዳጅ ነህ ሰው የራቀውን ምትጠጋ የልቡን በር ዘልቀህ ገብተህ ጨለማውን ምታነጋ መድኃኒት ሆንካት ለነፍሴ እስራቴን ፈታህና በማዕድህ አስቀመጥከኝ እኔም ባንተ ታሰብኩና ክበርልኝ /8/ የኔ መዝሙር የኔ ዜማ የኔ ልቅሶ የኔ እምባ ምስጋናን ቢጨምር እንጂ አንተስ ከጥንት የተቀባህ ንግግሬ ብቻ አይደለም እርምጃዬም ያስደስትህ እኔ ያለ ልክ ዝቅ ልበል አንተ ያለ ልክ ከፍ በል ቢልቃጡ ተሰብሮ.... ገና ከጥንት ስትመራኝ ስትመክረኝ አውቅሃለሁ ዛሬ ቤቴ ልትገባ ተራ ደርሶኝ ታስቤያለሁ ሳልወድህ እየወደድከኝ አኔ ታዲያ ምን እላለሁ ቤቴ ባንተ ካማረልኝ ነፍሴን ፊትህ አፈሳለሁ ክበርልኝ /8/ ቢልቃጡ ተሰብሮ....

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Asrat Mulachew

See all 13 songs by Asrat Mulachew