Gubae

አመልክሃለሁ

Amelkehalehu

አስራት ሙላቸው · ሕይወትህ ሕይወቴ · 2017

Amelkehalehu is an Amharic mezmur (worship song) by Asrat Mulachew, from the album Hiwoteh Hiwotie (2017).

አንት ከከበርክ እኔ ምን እሻለሁ ያንተ መክበር ያ የኔ ደስታ ነው ዘላለም አመልክሃለሁ ዘመኔን ላንተ ኖራለሁ ድምፅህን ስሰማው እጅግ ደስ ይለኛል ሽር ጉድ ስልልህ ክብር ይሰማኛል ረሃቤም ጥማቴም ፈቃድህን ማድረግ ነው ፃድቁን አይቼ ጠግቤ መኖር ነው ዘላለም አመልክሃለሁ ዘመኔን ላንተ ኖራለሁ /4/ ሙሽራው ሲከብር ደስ እንዲለው ሚዜ ደስታዬ ይሞላል ከብረህ ሳይህ ጊዜ ድመቅ በሁሉ ላይ ታይልኝ ቀን ሙሉ ፍጥረታት ሁሉ አይተው ጌታዬ ይበሉ ክብር ይሁን በላይ ክብር ይሁን በሰማይ በፍጥረት ሁሉ ላይ አንተ ብቻህን ታይ ክብር ይሁን በታች ክብር ይሁን በምድር በእጆች ስራ ላይ አንተ ብቻ ክበር ዘላለም አመልክሃለሁ ዘመኔን ላንተ ኖራለሁ /4/

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Asrat Mulachew

See all 13 songs by Asrat Mulachew