Gubae

አይረሳም

Ayresam

ቴዎድሮስ ታደሰ · ዋ

Ayresam is an Amharic mezmur (worship song) by Teodros Tadesse, from the album Wa.

ምን ጊዜም ማይረሳው ልቤ   ለእኔ ያረገው ውዴ   ብዘምረው ብዘምረው   ውለታው ብዙ ነው ( 2x) ተስፋ ቢስ ነበርኩ እኔማ ሞቴን የናፈኩኝ ጨለማ ወርሶት ሕይወቴን መኖር የታከተኝ አትሞትም በሕይወት ኑር አለኝ ከሰማይ ድምጽ መጣ ድቅድቁ ሌሊት ነጋልኝ ለእኔም ፀሐይ ወጣ ተዘርዝሮ አያልቅም ኢየሱስ ችርነቱ ከአይምሮ በላይ ነው በዝቷል ደግነቱ ቢወራ ቢነገር የማይሰለቸኝ የእርሱ ምሕረት ነው ደግፎ ያቆመኝ እኔማ አልችልም እንባ ይቀድመኛል ብዙ ብዙ ነገር ትዝ ትዝ ይለኛል እኔማ አልችልም እንባ ይቀድመኛል ብዙ ብዙ ነገር ትዝ ትዝ ይለኛል ምን ጊዜም ማይረሳው ልቤ   ለእኔ ያረገው ውዴ   ብዘምረው ብዘምረው   ውለታው ብዙ ነው ( 2x) በሰው ዓይን የማይሞላውን ሞገስን ያጠገበው ከተዋረደ ስፍራ ላይ ከትቢያ ላይ ያነሳው አይገርምም ቢያገለግለው ቢልለት ጐንበስ ቀና ምሕረቱ የገነነለት ምስክር ነውና ተዘርዝሮ አያልቅም ኢየሱስ ችርነቱ ከአይምሮ በላይ ነው በዝቷል ደግነቱ ቢወራ ቢነገር የማይሰለቸኝ የእርሱ ምሕረት ነው ደግፎ ያቆመኝ እኔማ አልችልም እንባ ይቀድመኛል ብዙ ብዙ ነገር ትዝ ትዝ ይለኛል እኔማ አልችልም እንባ ይቀድመኛል ብዙ ብዙ ነገር ትዝ ትዝ ይለኛል

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Teodros Tadesse

See all 37 songs by Teodros Tadesse