Gubae

ጌታ ለኔ ያደረግከው

Gieta Lenie Yaderekew

ነፃነት አሰፋ · እግዚአብሔርን ባርኪ

Gieta Lenie Yaderekew is an Amharic mezmur (worship song) by Netsanet Assefa, from the album Egziabhieren Barki.

ጌታ ፡ ለኔ ፡ ያድረከው ፡ ልቆጥረው ፡ አልችልም ፡ ወለታህ ፡ ብዙ ፡ ነው   ኢየሱስ ፡ ስለወደድ ፡ እወድሃለሁኝ ፡ አከብረሃለሁኝ ፡ ተመስገን ፡ እያልኩኝ ሳላውቅህ ፡ አውቀኸኝ ፡ ሳልወድህ ፡ ወድኸኝ በምረትህ ፡ ከበህ ፡ ቤትህ ፡ አኖርከኝ ከነፍሴ ፡ ምሥጋና ፡ ለአንተ ፡ እሰዋለሁ ምህረት ፡ ቸርነትህን ፡ እናገራለሁ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ አልታዘዝም ፡ ስል ፡ በደሌን ፡ ታግሰህ በፍቅርህ ፡ ገመድ ፡ ወዳንተ ፡ መልሰህ ስወድቅ ፡ አንስተኸኝ ፡ ስዝልም ፡ ደግፈህ እዚህ ፡ አደረሰከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ልበልህ የሚመስልህ ፡ የለም ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ለዘለዓለምም ፡ የማትተወኝ በዘለዓለም ፡ ፍቅርህም ፡ የወደድከኝ ጌታ ፡ ኢየሱሴ ፡ የነፍሴ ፡ እረኛ ወዳጄ ፡ ነህ ፡ ለኔ ፡ የማትተኛ የማትለየኝ ፡ ስነቃም ፡ ስተኛ አትለዋውጥም ፡ ሁልጌዜ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ፈጥነህ ፡ ትደርሳለህ ፡ ስምህን ፡ ለሚጠሩህ ኢየሱስ ፡ አምባዬ ፡ ለኔ ፡ መጠጊያዬ ዞሮ ፡ መግቢያዬ ፡ ነህ ፡ መሸሸጊያዬ ከመከራ ፡ ሁሉ ፡ መዳኛዬ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Netsanet Assefa

See all 40 songs by Netsanet Assefa