Gubae

የሚመስልህ የለም

Yemimesleh Yelem

ነፃነት አሰፋ · እግዚአብሔርን ባርኪ

Yemimesleh Yelem is an Amharic mezmur (worship song) by Netsanet Assefa, from the album Egziabhieren Barki.

የሚመስልህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ ፡  የሚመስልህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ ድንቅ ፡ ነህ  የሚመስልህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ  የሚመስልህ ፡ የለም ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ምህረትህ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ከሕይወት ፡ ይሻላል ፍቅርህም ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ እንደሞት ፡ ይበረታል ትዕግሥትህ ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ ዘመናት ፡ ያልፋል እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ በክብር ፡ ተቀምጠሃል እግዚአብሔር ፡ ብርሃን ፡ ነህ ፡ ብርሃንን ፡ ለበሰሃል በቃልህ ፡ ሰማይን ፡ ምድር ፡ ፈጥረሃል ኤልሻዳይ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ ተመለከታለህ ከቅዱስ ፡ ማደሪያ ፡ ትህዛዝ ፡ ትሰጣለህ ፍጥረትን ፡ በሙሉ ፡ አንተ ፡ ትገዛላህ ሰማይት ፡ ክብርህን ፡ ይናገራሉ ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ ድምጽህን ፡ ይሰማሉ ፡ ለቃልህ ፡ በፍርሃት ፡ ይታዘዛሉ ክብርን ፡ በሙሉ ፡ ለአንተ ፡ ያመጣሉ እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ የለም ፡ የሚመስልህ እጅግ ፡ ከፍ ፡ ያልክ ፡ ነህ ፡ በግርማ ፡ ሞገስህ ሰው ፡ በኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ አንተን ፡ ይቀርብሃል በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ ደግሞ ፡ ይሰግድልሃል

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Netsanet Assefa

See all 40 songs by Netsanet Assefa