Gubae

ክብር በሉት ኢየሱስን

Keber Belut Eyesusen

ነፃነት አሰፋ · ኢየሱስ ፍቅር

Keber Belut Eyesusen is an Amharic mezmur (worship song) by Netsanet Assefa, from the album Eyesus Feqer.

ለናዝሬት ፡ ኢየሱስ ፡ እንደበግ ፡ ለታረደው በደሙ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ሰዎችን ፡ ለዋጀው ለአምላክ ፡ መንግሥትና ፡ ካህናት ፡ ላደረገው ፡ በረከትና ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው   ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን   ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ያለና ፡ የነበር ፡ የሚመጣው ፡ ሁሉን ፡ የሚገዛው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው አእላፋት ፡ መላእክት ፡ ያከብሩታል ፡ ተመስገን ፡ እያሉ ፡ ይሰግዱለታል   ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን   ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ዛሬ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ የምሥጋናችን ፡ ቀን መርገምን ፡ አርቆዋል ፡ ሰርታል ፡ ስራችንን በፍፁም ፡ ፈቃዱ ፡ እንዲሁ ፡ አድኖናል ስገድትም ፡ ምሥጋናም ፡ ለእርሱ ፡ ያንስበታል  ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን  ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ መጀመሪያው ፡ የሁሉ ፡ ፍጻሜ ፡ መጨረሻው የሚመጣው ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የዓለምን ፡ ሃጥያት ፡ ያስወገደው   ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን   ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ባባቱ ፡ ቀኝ ፡ ላለው ፡ ለጌታ ፡ ለኢየሱስ ፡ አምልኮ ፡ ዝማሬ ፡ ከልባችን ፡ ይፍሰስ በክብር ፡ ታጅቦ ፡ በደመና ፡ ይመጣል ፡ ያለም ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ለክብሩ ፡ ይሰግዳል   ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን   ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው ፡ ክብር ፡ እንስጠው ፡ ይገባዋል ፡ ስግደት ፡ እናክብረው በምሥጋና ፡ ዜማ ፡ በዕልልታ ፡ በፊቱ ፡ እንዘምር ፡ በደስታ   ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡ ኢየሱስን   ክበር ፡ በሉት ፡ አሜን ፡ ክበር ፡ በሉት ፡

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Netsanet Assefa

See all 40 songs by Netsanet Assefa