Gubae

መንገድ አለው ጌታ

Menged Alew Gieta

ነፃነት አሰፋ · አለኝ ብዙ ምስጋና

Menged Alew Gieta is an Amharic mezmur (worship song) by Netsanet Assefa, from the album Alegn Bezu Mesgana.

መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታ ፡ እርሱ ፡ መንገድ ፡ አለው   መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታዬ ፡ እርሱ ፡ መንገድ ፡ አለው   መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታ ፡ እርሱ ፡ መንገድ ፡ አለው   መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታዬ ፡ እርሱ ፡ መንገድ ፡ አለው ባሕርን ፡ የሚከፍል ፡ ንፋስን ፡ ያመጣል ውሃውን ፡ አስወግዶ ፡ መንገድ ፡ ያደርገዋል ኃይለኛውንም ፡ ወንዝ ፡ እርሱ ፡ ያቆመዋል ደርቅ ፡ መንግድ ፡ አድርጐ ፡ ማሻገር ፡ ይችላል  ፡ በእግዚአብሔር ፡ ተስፋ ፡ አይቆረጥም  ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ የሚሳነው ፡ የለም ተራራውን ፡ አዞ ፡ ይደለድለዋል ሸለቆውን ፡ ከፍ ፡ አድርጐ ፡ መንገድ ፡ ያደርገዋል የእግዚአብሔር ፡ መንገድ ፡ በቀን ፡ ብቻ ፡ አይደለም ሌሊቱም ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ጨለማ ፡ አይሆንም  ፡ በእግዚአብሔር ፡ ተስፋ ፡ አይቆረጥም  ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ የሚሳነው ፡ የለም ደመናም ፡ ባይታይ ፡ ነፍሱም ፡ ባይነፍስም ለመጽናናት ፡ የሚሆን ፡ ምልክት ፡ ባይኖርም መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታ ፡ ውሃውን ፡ ያመጣል የሌለውን ፡ ጠርቶ ፡ ማኖር ፡ ያውቅበታል  ፡ በእግዚአብሔር ፡ ተስፋ ፡ አይቆረጥም  ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ የሚሳነው ፡ የለም

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Netsanet Assefa

See all 40 songs by Netsanet Assefa