Gubae

ስራህ ግሩም

Serah Gerum

ህሊና ካሳሁን · እግዚአብሔር ትልቅ

Serah Gerum is an Amharic mezmur (worship song) by Hillina Kassahun, from the album Egziabhier Teleq.

ስራህ ግሩም (Track 12) (ግሩም፣ ግሩም፣ ግሩም እና ድንቅ….. ነህ እግዚአብሔር ) አሻግርሻለሁ ስትል የታመንከው በራስህ ጉልበት በራስህ ጉልበት እኔ አቆምሻለሁ ስትል የታመንከው በራስህ ጉልበት በራስህ ጉልበት ጥያቄ የለኝም ጥርጥር አይገባኝ ስራው የእኔ እኮ ነው ብለኸኛል ታማኝ (2x) ኦሆ እግዚአብሔር ድንቅ ነህ ኦሆ ክንድህን አይቻለሁ ኦሆ የደነደነውን ልብ ኦሆ እንደሰም ስታቀልጠው ኦሆ ነፍሴ ተማርካለች ኦሆ እስከለዘላለም ኦሆ ከሀሳብህ ውጪ ኦሆ የሚወስደኝ የለም ስራህ ግሩም እና ድንቅ ነው (3x) እኔ እላለሁ ክብርህ ግሩም እና ድንቅ ነው (3x) እኔ እላለሁ አቤት በሰራኸው ባደረከው ሁሉ እጅግ ተደንቄ ተገርሚያለሁ ክብርህን ስትገልጥ ዝናህን ስታሳይ አጋዥ አትፈልግም አንት የሌለህ ከልካይ ባደረከው ሁሉ በሰራህልኝ ከተመስገን ሌላ የምለው የለኝ ነገር ግን በፊትህ በክብርህ ውስጥ ሆኜ ጌታ እልሀለሁ... ስራህ ግሩም እና ድንቅ ነው (3x) እኔ እላለሁ ክብርህ ግሩም እና ድንቅ ነው (3x) እኔ እላለሁ ኦሆ ሰማያት ክብርህን ኦሆ ክብርህን ያወራሉ ኦሆ ፍጥረታትም ደግሞ ኦሆ ይመሰክራሉ ኦሆ እነርሱ ገብቷቸው ኦሆ ይገባዋል ካሉ ኦሆ እኔ እኔማ እንዴት አልል ኦሆ ስራህ ግሩም ስራህ ግሩም እና ድንቅ ነው (3x) እኔ እላለሁ ክብርህ ግሩም እና ድንቅ ነው (3x) እኔ እላለሁ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Hillina Kassahun

See all 13 songs by Hillina Kassahun