Gubae

ቀሪ

Qeri

ህሊና ካሳሁን · እግዚአብሔር ትልቅ

Qeri is an Amharic mezmur (worship song) by Hillina Kassahun, from the album Egziabhier Teleq.

ቀሪ (Track 7) ቀሪ ቀሪ ሀብቴ ትርፍ ድርሻ ክፍያ ዋጋዬ አንተ አይደለህም ወይ (4x) በዙፉንህ ላይ ተቀምጠህ ምድርና ሞላዋን በጅህ ይዘህ የምትኖር አንተ ባለግርማ እጠብቅሀለሁ ቀንና ቀንና ማታ በዙፉንህ ላይ ተቀምጠህ ምድርና ሞላዋን በጅህ ይዘህ የምትኖር አንተ ባለግርማ ትናፍቀኛለህ ቀንና ቀንና ማታ እጠብቅሀለሁ ቀንና ቀንና ማታ (2x) ትናፍቀኛለህ ቀንና ቀንና ማታ ትናፍቀኛለህ አዝለህ ተሸክመህ እዚህ ያቆምከኝ በምድረበዳም ውስጥ ለነፍሴ ውሀ የሆንከኝ አጥንቶቼንም ያበረታሀቸው ለካ ትበቃለህ ሌላው ከንቱ ነው ምድር ሁሉ ሲነዋወጥ የወለደ ሲረሳ ለአንድ ቀን አተወኝም የኔ ታማኝ እረኛ ምድር ሁሉ ሲነዋወጥ የወለደ ሲረሳ ለአንድ ቀን አትጥለኝም የኔ ታማኝ እረኛ ምንም እንኳን በለስ ባታፈራ በወይንም ሀረግ ፍሬ ባይገኝም የማልፍበት መንገድ ባይገባኝም የዚህ ምድር ጉዞ ከቶ አያሰጋኝም አይኖቼ ወደከፍታ ወዳለክበት ስፍራ አትኩረው ያዩሀል ደግመህ እስከምትመጣ (2x) በዙፉንህ ላይ ተቀምጠህ ምድርና ሞላዋን በጅህ ይዘህ የምትኖር አንተ ባለግርማ እጠብቅሀለሁ ቀንና ቀንና ማታ በዙፉንህ ላይ ተቀምጠህ ምድርና ሞላዋን በጅህ ይዘህ የምትኖር አንተ ባለግርማ ትናፍቀኛለህ ቀንና ቀንና ማታ እጠብቅሀለሁ ቀንና ቀንና ማታ (2x) ትናፍቀኛለህ ቀንና ቀንና ማታ ትናፍቀኛለህ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Hillina Kassahun

See all 13 songs by Hillina Kassahun