Gubae

አስረሳኝ

Asresagn

ህሊና ካሳሁን · እግዚአብሔር ትልቅ

Asresagn is an Amharic mezmur (worship song) by Hillina Kassahun, from the album Egziabhier Teleq.

አስረሳኝ የድሮውን አስረሳኝ የባከነውን ዘመናት እንባዬን የፈሰውን አስረሳኝ እንዳልነበረ አሳቀኝ ህይወቴን ቀየረ/2 ኧረ እንዴት አይነት ቸር ነው እኔን የወደደው እንዴ ምን አይነት ፍቅር ነው እኔን የመረጠው/2 ያጠፋሁት ዘመን ስጋዬን ታምኜ የጠቀመኝ መስሎኝ እጅጉን ታልዬ እንዲሁ ስባክን መሰዊያዬን ትቼ ምህረትህ አገኘኝ ባዶዬን ቀርቼ መጣሁ እጄን ሰጥቼ አለቀ አበቃ ባልኩበት በሃር ላይ በሃይልህ ተገለጥክ የእኔ ተበቃይ ህይወትን ልትዘራ በሞተው ነገር ላይ አላስቻለህ ልብህ የእኔን እንባ ስታይ ወደድክ ልትመጣ ከላይ ኧረ እንዴት አይነት ቸር ነው እኔን የወደደው እንዴ ምን አይነት ፍቅር ነው እኔን የመረጠው/2 የምርጦቹ ምርጦች ቢሰበሰቡለት እውቀት የተካቡት ቢመሰክሩለት እንኯን ሊመጥነው ፈፅሞም አይገልፀው ታዲያ እኔ ምንድን ነኝ ባይኑ የምታየው ይሄስ እውነት ፍቅር ነው አስረሳኝ የድሮውን አስረሳኝ የባከነውን ዘመናት እንባዬን የፈሰውን አስረሳኝ እንዳልነበረ አሳቀኝ ህይወቴን ቀየረ/2 ኧረ እንዴት አይነት ቸር ነው እኔን የወደደው እንዴ ምን አይነት ፍቅር ነው እኔን የመረጠው/2

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Hillina Kassahun

See all 13 songs by Hillina Kassahun