Gubae

አላማርረውም

Alamarerewem

ዳንኤል አምደሚካኤል · ይሆናል · 2003

Alamarerewem is an Amharic mezmur (worship song) by Daniel Amdemichael, from the album Yehonal (2003).

ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል ርዕስ አላማርረውም አልበም ይሆናል አዝ ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ባይሞላ በዚህ አልመዝነውም ከሁኔታዎች በላይ ነው ማንም አይከሰውም (፪x) አቤት የእኔ ጌታ አሰራሩ ግሩም የዘገየ ሲመስል ማንም አይቀድመውም ቢሆንም ባይሆንም ለእኔ ፀጋው ይበቃኛል ቢሆንም ባይሆንም ለእኔ ፍቅሩ ይበቃኛል አዝ ነገር ቢሞላ ባይሞላ በዚህ አልመዝነውም ከሁኔታዎች በላይ ነው ማንም አይከሰውም (፪x) ሁልጊዜ መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ እግሬን በቤቱ ለእኔስ ፍቅሩ ይበቃኛል እንደ እግዚአብሔር ከየት ይገኛል እርሱ ነው የእኔ እድል ፈንታ እርስቴ የሕይወቴ መከታ ሁልጊዜ በእርሱ ደስ ይለኛል ከሁሉ ፍቅሩ በልጦብኛል አዝ ነገር ቢሞላ ባይሞላ በዚህ አልመዝነውም ከሁኔታዎች በላይ ነው ማንም አይከሰውም (፪x) አቤት የእኔ ጌታ አሰራሩ ግሩም የዘገየ ሲመስል ማንም አይቀድመውም ቢሆንም ባይሆንም ለእኔ ፀጋው ይበቃኛል ቢሆንም ባይሆንም ለእኔ ፍቅሩ ይበቃኛል የሰው ፍላጐቱ ብዙ ነው የእግዚአብሔርን ፍቃድ እስኪለየው በልቤ ብዙ ሃሳብ ይኖራል የእግዚአብሔር የሆነው ይፀናል ይፀናልኝ ለእኔስ የእርሱ ሃሳብ ፈቃዱን ለመጣስ አልሻም ሃሳቤን የእርሱ ሃሳብ ይወረሰው ሲገለጥ ሁሉም ለበጐ ነው ተግቶ ለጠበቀው ጌታ ሲሰጥ ምላሹን ለምን ተስፋ ልቁረጥ ሳልዘልቅ በትንሹ መታገስ ጥሩ ነው ብዙ ድንቅን ያሳያል ፀንቶ የጠበቀ መልካም ፍሬ ይበላል ከሁሉ የበለጠ ክብሩን አይቻለሁ ወደር የለሽ ፍቅሩን ምሕረት አግኝቻለሁ በትልቅ ትንሹ እንዴት አማርራለሁ የተደረገልኝ እጅግ እጅግ ብዙ ነው።

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Daniel Amdemichael

See all 64 songs by Daniel Amdemichael