Gubae

ላምላክነትህ

LeAmlaknetih

ቤተልሔም ወልዴ · እረኛዬ

LeAmlaknetih is an Amharic mezmur (worship song) by Bethlehem Wolde, from the album Eregnaye.

ላምላክነትህ እንሰግዳለን ለጌትነትህ እንዘምራለን ክቡር ክቡር ክቡር ነህና ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነህና (2X) ለኛስ ውለታህ ስለበዛብን የማይገባንን ከፍ ክፍ ካረከን በልጅህ ምክንያት ወዳንተ ቀርበናል ክቡር ነህ እግዚአብሔር ተመስገን ብለንሀል (2X) ላምላክነትህ እንሰግዳለን ለጌትነትህ እንዘምራለን ክቡር ክቡር ክቡር ነህና ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነህና (2X) በላይ በሰማይ ተቀምጠህ ላለህው ብርሃንን እንደልብስ ለተጎናጸፍከው በእውነት በመንፈስ እንሰግድልሃለን ስምህን በዝማሬ እንወድሰዋለን የፈጠርካቸውም አንተን ይጠሩሀል ጠዋትና ማታ ክብርን ይሰጡሀል አሁንም ተባረክ ስምህ ይባረክ በእጆችህ ስራ ዛሬም ተወደስ ላምላክነትህ እንሰግዳለን ለጌትነትህ እንዘምራለን ክቡር ክቡር ክቡር ነህና ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነህና (2X)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Bethlehem Wolde

See all 33 songs by Bethlehem Wolde