Gubae

እረኛዬ

Eregnaye

ቤተልሔም ወልዴ · እረኛዬ

Eregnaye is an Amharic mezmur (worship song) by Bethlehem Wolde, from the album Eregnaye.

እረኛዬ አንተ የኔ እረኛ የነፍሴ ጠባቂ አንተ የማትተኛ እኮራለሁ ባንተ እመካለሁ በምንም አልፈራም በምንም አልሰጋም  የነፍሴ ንጉስ ኢየሱስ አንተ ለኔ እረኛዬ ነህ   ነፍሴን ከአዳኝ ወጥመድ ዘወትር ትጠብቀኛለህ  አንተ የኔ እረኛ አትተኛም አታንቀላፍም  በሰላም ውዬ አድራለሁ እኔ በምንም አልሰጋም እረኛዬ አንተ የኔ እረኛ………  ካንተ ሌላ ወዳጅ ካንተ ሌላ እረኛ  ለኔስ ምንም የለኝ አንተ የማትተኛ  መልካም እረኛ ኢየሱስ ስለኔ ነፍሱን ሰጥቶኛል  ሰላሙ ልቤን ሞልቶ በድል ያራምደኛል እረኛዬ አንተ የኔ እረኛ………  በለመለመ መስክ ዘወትር ያሳድረኛል   በእረፍት ውሀ ዘንድ ጌታ እኔን ይመራኛል   ቸርነት ምህረቱ እየተከተሉኝ   ከክፉ ይጠብቁኛል በድል ያራምዱኛል እረኛዬ አንተ የኔ እረኛ………  ምድር ብትነዋወጥ ብትነዋወጥ  ሁሉም ነገር ስፍራውን ቢለቅ  ከቶ እንዳልፈራ ከቶ እንዳልናወጥ  ልቤን ሞላኸው በሰላም በእረፍት  ያረጋጋኸኝ በነውጡ አለም  ጋሻዬ ነህና ለዘለአለም  እኔ ልበልህ እረድኤቴ  ስለሆንክልኝ አቅም ጉልበቴ  እልሀለሁ እረድኤቴ(6x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Bethlehem Wolde

See all 33 songs by Bethlehem Wolde