Gubae

ይኑርልን ጌታ

Yinurelen Gieta

በረከት ለማ · ያቦቅን ስሻገር

Yinurelen Gieta is an Amharic mezmur (worship song) by Bereket Lemma, from the album Yaboken Seshager.

ያደርንበት ኃጢአት ከንስሃ ጣፍጦ እግዚአብሔርን መፍራት ተንቋል አመፅ በዝቶ አንዳችን በኃጢአት ከሌላው ለመላቅ ተፎካከርን ጌታን ከቤቱ ለማራቅ አይታገልም ጌታ ከአፍኒና ከፊንሃስ ጋራ ይርቃል እንጂ ከማይፈሩት ትራፊ እየሰጡ ከሚንቁት ኢካቦድ ሆኖ በሐገሪቱ በእልልታ ቢቀለጥ መንደሩ አደንድኗል አመፅ ልባቸውን እስኪሰጥ በጅራፍ ዋጋቸውን ና.. ባደባባይ ስምህ ተሰድቧል ና. ና መልሰን ፊትህ ወድቀናል ና.... የተወሰደው ክብር ይመለስ ና. ና አንተ ቆይልን ሚሄድ ይሂድ ሙሽራው እያለ ሎሌው ደምቆ ነውር የማይፈራ ምህረቱን ተለማምዶ ሙሽሪትም ደጇን ለሌላው ከፍታ በአላፊው አግዳሚው ጨረሰች ዘይቷን የለበትም ጌታ በምስባኩ በተዘጋዘጀው በስሙ ይሰበካል እንጂ የሰው ዝና ባሪው ከጌታው ልቋልና አይጠራም ኢየሱስ በመድረኩ አይነገርም ከቶ ትምህርቱ ይሰበካል እንጂ ታምራቱ ለንግድ የሚሆን ጥራዝ ጥቅሱ ይኑርልን ጌታ በቤቱ ይሰንብት ለርስቱ ሚፈልገው አለ ከነፍሱ የማይኖር ያለ እሱ ባይተዋር አናርገው አንግፋው ይኑርልን ጌታ ዝም ማለቱን አንናቅ ምህረቱ ሲበዛ ላይ ላያችን ሲታይ ጣዖት ተፀያፊ በቤተ መቅደስ ግን ከእግዜር እጅ ዘራፊ በድፍረት ልምምድ ጌታን ስንጋፋ የምህረት ደጁን እግዜር እንዳይዘጋ ና.. ባደባባይ ስምህ ተሰድቧል ና. ና መልሰን ፊትህ ወድቀናል ና.... የተወሰደው ክብር ይመለስ ና. ና አንተ ቆይልን ሚሄድዉ ይሂድ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Bereket Lemma

See all 13 songs by Bereket Lemma