Gubae

ከተባለ ለአንተ

Ketebale Lante

በረከት ለማ · ያቦቅን ስሻገር

Ketebale Lante is an Amharic mezmur (worship song) by Bereket Lemma, from the album Yaboken Seshager.

የዛሬ ቀን አይተህልኝ እጄን የያዝክ ከልጅነቴ የት ይደርሳል ብለህ ያልናቅከኝ ስትደግፈኝ እዚህ አደረስከኝ አባት ነህ የአባት ልኩ ወዳጅ ነህ የወዳጅ ልኩ አልተውከኝም እስካሁን እድሜ ተሸክመኸኛል ጥላ ሆነህ አጥሬ ከተባለ ላንተ ምስጋና ኧረ ብዙ ነው እኔ ቤት ና ከተባለ ላንተ አምልኮ እንደ ዳዊት ነው ማመልክህ እኮ ልክ እስከማይኖረኝ ገደብን እስካጣ ሜልኮል እስክትታዘበኝ አምልኮዬ ዛሬም ይበዛል ያ ባለዝና ያ ባለዘውድ አንተ ባትጨመርበት ማን ይለው ነበር ንጉስ ዳዊት ያ ባለዘውድ ያ ባለዝና ከሆነው በላይ ቢሆን ቢያንስበት እንጂ መች ይበዛና ከበዛልኝ ምህረት ከቸርነትህ አንዳች ማይገባኝ ደካማ ነበርኩኝ በእኔ ጉልበት ሳይሆን በራስህ ተማምነህ እንዳለፈ ውሃ ስንቱን አስረሳኸኝ ካረክልኝ ከሆንክልኝ ሚተካከል ቃል ባይገኝም አምልኮዬ ዝማሬዬ ዙፋንህን ይክበብልኝ ዝማሬዬ ይክበብልኝ ፡ እልልታዬ ይክበብልኝ ዝማሬዬ ይክበብልኝ ፡ አድናቆቴ ይክበብልኝ ለመመረጥ ለመታሰብ ያልታደለ በሰው ፊት ወዳጅ ሆንከው በቤቱ ገባህ በጠለት ፊት እራሱን ቀባህ አባት ነህ የአባት ልኩ ወዳጅ ነህ የወዳጅ ልኩ አልተውከኝም እስካሁን እድሜ ተሸክመኸኛል ጥላ ሆነህ አጥሬ ከተባለ ላንተ ምስጋና ኧረ ብዙ ነው እኔ ቤት ና ከተባለ ላንተ አምልኮ እንደ ዳዊት ነው ማመልክህ እኮ ልክ እስከማይኖረኝ ገደብን እስካጣ ሜልኮል እስክትታዘበኝ አምልኮዬ ዛሬም ይበዛል

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Bereket Lemma

See all 13 songs by Bereket Lemma