Gubae

መንገዴን አደራ

Mengedien Adera

አገኝሁ ይደግ · ኃይለኛ እንዳንተ የለም · 1992

Mengedien Adera is an Amharic mezmur (worship song) by Agegnehu Yideg, from the album Haylegna Endante Yelem (1992).

ባለፈው ዘመኔስ ብዙ አጥፍቻለው ባለማስተዋሌም ተጎድቻለው ፍቅርን የተሞላህ ባታግዘኝ ኖሮ እንዴት ይዘለቃል የዚህ ምድር ኑሮ አሁንም ጌታዬ መንገዴን አደራ ታዳጊ አንተ ነህ በሚገጥመኝ መከራ (2) አዝ፦ መንገዴን አደራ አደራ በቀረው ዘመኔስ ስራህን ስራ (2) ጉዞዬ ከብዶብኝ ስወድቅ ስነሳ እዚህ ደርሻለው በብዙ አበሳ የቀረው ዘመኔስ ብሩህ ይሁንልኝ ኢየሱሴ በኃይልህ ስራዬን ስራልኝ የኋላዬን ልርሳ ወዳንተ ልጠጋ ከፊቴ ያለውን ለመያዝ ልዘርጋ አዝ፦ መንገዴን አደራ አደራ በቀረው ጉዞዬስ ስራህን ስራ(2) በስጋዬ ምኞት በከንቱ ስገዛ ስንት ጊዜ አቃጠልኩ እንዲሁ በዋዛ ለቅዱሱ አደራህ ታማኝ አልነበርኩም እንደልብህ ደስታም አላገለገልኩም እንግዲህስ ጌታ ስራብኝ እንደሰው (በጭንጋፉ) በትንሹ ባሪያ ከሁሉም በማንሰው

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Agegnehu Yideg

See all 51 songs by Agegnehu Yideg