Gubae

ማነው ሰላም የሌለው

Manew Selam Yelielew

አገኝሁ ይደግ · ኃይለኛ እንዳንተ የለም · 1992

Manew Selam Yelielew is an Amharic mezmur (worship song) by Agegnehu Yideg, from the album Haylegna Endante Yelem (1992).

ሰላሳ ስምንት አመት ባልጋ ላይ ተኝቼ ተኝቼ ወደ ፈውስ ቦታ የሚያደርሰኝ እንድም ሰው አጥቼ የነፍሴን መጎዳት ብቸኝነቴን ኧረ ማን አየልኝ ማን አየልኝ የሱሴ ብቻ ነው የደረሰልኝ ዛሬስ ይብቃህ ያለኝ ይክበርልኝ ከእንግዲህ ምን እላለሁኝ በእግዚአብሔር ከታየሁኝ ይኸው ለክብሩ አዜማለሁኝ/2 ማነው ሰላም የሌለው የሱስን አሁን ይከተለው ማነው እረፍት የራቀው የሱስን እኔ ላስተዋውቀው አስራ ሁለት አመት ከሰው ተገልዬ እጅግ ደም ሲፈሰኝ ሲፈሰኝ በሽታዬ ላይድን ዝም ብሎ ገንዘብ ሲያስጨርሰኝ ወደ እየሱስ መጣው ተጋግጬ ጨርቁን ዳሰስኩኝ ዳሰስኩኝ ሃይልም ከሱ ወጣች እኔም እንደሰው ፈውስ አገኘሁኝ ይክበርልኝ ከእንግዲህ ምን እላለሁኝ በእግዚአብሔር ከታየሁኝ ይኸው ለክብሩ አዜማለሁኝ/2 ማነው ሰላም የሌለው የሱስን አሁን ይቀበለው ማነው ወዳጅ የራቀው የሱስን እኔ ላስተዋውቀው በስምዖን ቤት ውስጥ እንዳለ ወሬ ሰማሁኝ ሰማሁኝ ከሃጥያት በሽታ ለመዳን ስሮጥ ገባሁን ከእግሩ ስር ወድቄ ማረኝ አልኩኝ ስቅስቅ እያልኩኝ አለቀስኩኝ በብዙ ወደድኩት በብዙ ማረኝ ወደ እርሱ አስጠጋኝ ይክበርልኝ ከእንግዲህ ምን እላለሁኝ በእግዚአብሔር ከታየሁኝ ይኸው ለክብሩ አዜማለሁኝ/2 ማነው ሰላም የሌለው የሱስን አሁን ይቀበለው ማነው ጤና የራቀው የሱስን እኔ ላስተዋውቀው በሞት እንቀጣ ተፈርዶብኝ ከጉንይ ሰቅለውኝ ሰቅለውኝ ይሄ ሰው ፃድቅ ነው ሃጥያት የለበትም ብዬ ተናገርኩኝ በእውነት እልሃለው ዛሬ በገነት ከኔ ጋር ነህ አለኝ ነህ አለኝ እስራኤል አለና ስሜን ለወጠልኝ ከመሞት አዳነኝ ይክበርልኝ ከእንግዲህ ምን እላለሁኝ በእግዚአብሔር ከታየሁኝ ይኸው ለክብሩ አዜማለሁኝ/4

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Agegnehu Yideg

See all 51 songs by Agegnehu Yideg