ኃይለኛ እንዳንተ የለም
Haylegna Endante Yelem
አገኝሁ ይደግ · ኃይለኛ እንዳንተ የለም · 1992
Haylegna Endante Yelem is an Amharic mezmur (worship song) by Agegnehu Yideg, from the album Haylegna Endante Yelem (1992).
ከባርነት አገር ወደ አንተ ያመጣኸን ቀንበርን ሰባብረህ አርነት ያወጣኸን በጨለማ ያለ ህዝብ ታላቅ ብርሃን አየ ከሰቆቃ ኑሮ ከሴይጣን ተለየ አዝ ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ x2 እግዚአብሔር ኃያል ነህ ማንንም አትንቅም የሚጤሰውን ጧፍ አጥፍተህ አታውቅም ለደካማው ኃይልን ለጭንጋፉ ሞገስ አንተ ግን ጌታ ነህ ለዘለዓለም ንገሥ አዝ {ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ}x2 በሰማይ በምድር ከምድር በታች ሁሉ ማኅተሙን ሊፈቱ አንዳቸውም አልቻሉ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶቹ ጌታ አንተ ግን ችለሃል ማኅተሙን ፡ ልትፈታ አዝ {ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ}x2 ሞተሃል ተብሎ እኛም ተስፋ ቆርጠን በራችንን ዘግተን አዝነን ተቀምጠን አንተ ግን ልዩ ነህ ታሪክ ለውጠሃል ሞትና መውጊያውን ለዘለዓለም ሰብረሃል አዝ {ኃይለኛ ፡ እንዳንተ ፡ የለም ንገሥ ዘለዓለም ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ}x2 ትዕቢተኛውን ፈርዖን ሊያጠፋን ሲነሳ ዙሪያችንን ሲዞር ሊውጠን እንደ አንበሳ ቀድመህ ደረስክና አፉን ለጐምክልን ምን እንበላ ሌላ ለእኛስ ዘለዓለም ንገሥልን አዝ {ኃይለኛ እንዳንተ የለም ንገሥ ዘለዓለም ማህተሙን ኧረ ማን ፈታ ከፍ በል ጌታ} Big text


