Gubae

ለምን እፈራለሁ

Lemen Eferalehu

አገኝሁ ይደግ · ጨለማዬ በራ · 2012

Lemen Eferalehu is an Amharic mezmur (worship song) by Agegnehu Yideg, from the album Chelemayie Bera (2012).

እግዚአብሔር ፡ እያለ ፡ ለምን/እንዴት ፡ እፈራለሁ አምናንም ፡ ካቻምናንም ፡ ሁሉን ፡ አይቻለሁ አምናንም ካችአምናንም ክንዱን አይቻለሁ (፪x) ሸለቆ ተራራው ከፍታው ዝቅታው አቤት ከእርሱ ጋራ ከፊት ከፊት ሲሄድ እጄን ይዞ እኔን እየመራ አዎ አይቸዋለሁኝ ጥበቃውን ምህረቱን ለልጁ እንዳበዛ ዛሬም ቢሆን አምነዋለሁ አይተወኝም እንዲሁ እንደ ዋዛ አዝ እግዚአብሔር እያለ ለምን እፈራለሁ አምናንም ካችአምናንም ክንዱን አይቻለሁ (፪x) ከእናቱ ቤት ከአባቱ ከዘመዱ አብርሃምን ብቻውን ጠራና እኔ ወደ ማሳይህ አገር ሂድ ብሎ አዘዘውና አዎ ቃልኪዳን ገባለት ሊባርከው ለዘሩ ምድርን ሊያወርሰው እንደ ተናገርው የብዙ ህዝብ አባት አደረገው አዝ እግዚአብሔር እያለ ለምን እፈራለሁ አምናንም ካችአምንም ክንዱን አይቻለሁ (፪x) በቃሉ ተናግሮኝ ጠብቄው በፀሎቴ ምንም አልነሳኝም አባት አለኝ ብዬ ተመክቼ አላሳፈረኝም አዎ በፍፁም አልሰጋም ትደላደልኩ በአባቴ ቤት እግሬ ተተከለ ነገም ለሚሆነው አልፈራም አማኑኤል አለ አዝ እግዚአብሔር እያለ ለምን እፈራለሁ አምናንም ካቻአምናንም ክንዱን አይቻለሁ አምናንም ካቻ አምናንም ክንዱን አይቻለሁ (፪x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Agegnehu Yideg

See all 51 songs by Agegnehu Yideg