Gubae

ነፍሴ አንተን አለች

Nefsie Anten Alech

አገኝሁ ይደግ · ጌታ እኮ ነው · 1993

Nefsie Anten Alech is an Amharic mezmur (worship song) by Agegnehu Yideg, from the album Gieta Eko New (1993).

ዘማሪ አገኘሁ ይደግ ርዕስ ነፍሴ አንተን አለች አልበም ጌታ እኮ ነው ከምድረ በዳው ኑሮ ከዛ ከቃጠሎ አንተ ነህ የታደካት ደርሰህላት ቶሎ ስለዚህም ነፍሴ አንተን አንተን አለች ቀንና ሌሊት ፊትህን ፈለገች አዝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ አንተን አንተን አለች (፬x) ኢየሱስ አንተ ነህ ለነፍሴ ትርጉሟ እውነተኛ ወዳጅ የኑሮ ጣዕሟ ያለ አንተ መኖር አይሆንላትም መጠጊያ ጐጆ ሌላ የላትም አዝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ አንተን አንተን አለች (፬x) ባስለመድከኝ ስፍራ እጠብቅሃለሁ አንተን ካላገኘሁ መቼ እተኛለሁ ሌሊቱ ጭር ብሏል ሰው ሁሉ ተኝቷል ከአንተ ጋር መሆኑ ነፍሴ ግን አምሯታል አዝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ ነፍሴ አንተን አንተን አለች (፬x) እግዚአብሔር አለቴ እመካብሃለሁ እስከ ዘለዓለሙ ተስፋ አደርግሃልሁ ምንም ሳትሰራልህ ነፍሴን ወደሃታል ለቀሪውስ ጉዞ ምንድን ያሰጋታል በእንባ አንተኑ ደጅ ልጥና በልጅህ አትጨክንምና በእንባ አባቴን ደጅ ልጥና ሌላ የለኝምና (፪x) አትጨክንምና ሌላ የለኝምና (፬x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Agegnehu Yideg

See all 51 songs by Agegnehu Yideg