Gubae

የሠራዊት ጌታ

Yeserawit Gieta

ተስፋዬ ጋቢሶ · እግዚአብሔር መንፈስ ነው

Yeserawit Gieta is an Amharic mezmur (worship song) by Tesfaye Gabisso, from the album Egziabhier Menfes New.

የሠራዊት ፡ ጌታ ፡ ኃያሉ ፡ መድህኔ ሲጠብቀኝ ፡ ሳለ ፡ ፍርድና ፡ ኩነኔ በኃጢአት ፡ ጣር ፡ ስኖር ፡ ተሳስሬ ከእስራቴ ፡ ፈታኝ ፡ መራኝ ፡ ወደ ፡ አገሬ (፪x) አዝ፦ በጭንቄ ፡ ተጨንቆ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ተሰቅሎ ላረባሁት ፡ ልጁ ፡ እንዲያ ፡ ተጐሳቁሎ ደሙን ፡ አፈሰሰ ፡ በፍቅሩ ፡ ተገዶ ሕይወቴን ፡ አዳናት ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተዋርዶ (፪x) ፍፁም ፡ የማልረባ ፡ ማስተዋል ፡ የሌለኝ አዳኜን ፡ የማላውቅ ፡ ፍርድ ፡ የሚጠብቀኝ የሰይጣን ፡ ምርኮኛ ፡ ሸክም ፡ የተጫነኝ እንዲህ ፡ ያለሁ ፡ ነበር ፡ ጌታ ፡ ሳያገኘኝ (፪x) አዝ፦ በጭንቄ ፡ ተጨንቆ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ተሰቅሎ ላረባሁት ፡ ልጁ ፡ እንዲያ ፡ ተጐሳቁሎ ደሙን ፡ አፈሰሰ ፡ በፍቅሩ ፡ ተገዶ ሕይወቴን ፡ አዳናት ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተዋርዶ (፪x) ፍርሃት ፡ መጠራጠር ፡ ክፋትና ፡ እርኩሰት ይወገድ ፡ ትዕቢት ፡ ቅናት ፡ ምቀኝነት ተንኮልና ፡ ውሸት ፡ ሀሜት ፡ ክፉ ፡ ምኞት ተደምስሰው ፡ ይጥፉ ፡ በጽዮኑ ፡ አለት (፪x) ይውደቁ ፡ ይፈጩ ፡ ይድቀቁ ፡ በአንድነት ቀንበሩ ፡ ተሰብሯል ፡ ይቅርብኝ ፡ ባርነት ዕዳዬም ፡ ተከፍሎ ፡ ታውጇል ፡ አርነት ሞትም ፡ አያስፈራኝ ፡ ተሰጥቶኛል ፡ ሕይወት (፪x) የሠራዊት ፡ ጌታ ፡ ኃያሉ ፡ መድህኔ ሲጠብቀኝ ፡ ሳለ ፡ ፍርድና ፡ ኩነኔ በኃጢአት ፡ ጣር ፡ ስኖር ፡ ተሳስሬ ከእስራቴ ፡ ፈታኝ ፡ መራኝ ፡ ወደ ፡ አገሬ (፪x) አዝ፦ በጭንቄ ፡ ተጨንቆ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ተሰቅሎ ላረባሁት ፡ ልጁ ፡ እንዲያ ፡ ተጐሳቁሎ ደሙን ፡ አፈሰሰ ፡ በፍቅሩ ፡ ተገዶ ሕይወቴን ፡ አዳናት ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተዋርዶ (፪x) ፍፁም ፡ የማልረባ ፡ ማስተዋል ፡ የሌለኝ አዳኜን ፡ የማላውቅ ፡ ፍርድ ፡ የሚጠብቀኝ የሰይጣን ፡ ምርኮኛ ፡ ሸክም ፡ የተጫነኝ እንዲህ ፡ ያለሁ ፡ ነበር ፡ ጌታ ፡ ሳያገኘኝ (፪x) አዝ፦ በጭንቄ ፡ ተጨንቆ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ተሰቅሎ ላረባሁት ፡ ልጁ ፡ እንዲያ ፡ ተጐሳቁሎ ደሙን ፡ አፈሰሰ ፡ በፍቅሩ ፡ ተገዶ ሕይወቴን ፡ አዳናት ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተዋርዶ (፪x) ፍርሃት ፡ መጠራጠር ፡ ክፋትና ፡ እርኩሰት ይወገድ ፡ ትዕቢት ፡ ቅናት ፡ ምቀኝነት ተንኮልና ፡ ውሸት ፡ ሀሜት ፡ ክፉ ፡ ምኞት ተደምስሰው ፡ ይጥፉ ፡ በጽዮኑ ፡ አለት (፪x) ይውደቁ ፡ ይፈጩ ፡ ይድቀቁ ፡ በአንድነት ቀንበሩ ፡ ተሰብሯል ፡ ይቅርብኝ ፡ ባርነት ዕዳዬም ፡ ተከፍሎ ፡ ታውጇል ፡ አርነት ሞትም ፡ አያስፈራኝ ፡ ተሰጥቶኛል ፡ ሕይወት (፪x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Tesfaye Gabisso

See all 75 songs by Tesfaye Gabisso