Gubae

አንተ ግን ጌታ ሆይ

Ante Gen Gieta Hoy

ተስፋዬ ጋቢሶ · ክርስቲያን ተሻገረ

Ante Gen Gieta Hoy is an Amharic mezmur (worship song) by Tesfaye Gabisso, from the album Christian Teshagere.

በተዘረጋ ፡ ክንድ ፡ በበረታችም ፡ እጅ በጌታ ፡ መዳኑን ፡ ከሞት ፡ ከሲዖል ፡ እጅ እንደምን ፡ ዘንግቶ ፡ ሰው ፡ ያጉረመርማል ወንድሙን ፡ ለመውገር ፡ እጁን ፡ ይዘረጋል አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈጦ ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ ጥርሱን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x) ስፍራውን ፡ ለቆ ፡ ሲሄድ ፡ ለመጉደፍ ፡ ሲቸኩል ትህትናውን ፡ አውልቆ ፡ ለሞት ፡ ሲንቀለቀል እዪት ፡ ያንን ፡ ዝንጉ ፡ ቃል ፡ ኪዳኑን ፡ ሲያፈርስ በአመጻው ፡ ብዛት ፡ ፍቅርን ፡ ሲያቀዘቅዝ አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈጦ ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ ጥፍሩን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x) አንተን ፡ እየፈራሁ ፡ ቀኑን ፡ ሁሉ ፡ ልኑር ትህትናም ፡ አይራቀኝ ፡ አልነፈግህ ፡ ክብር እጅህ ፡ እንዳይመታኝ ፡ አጉል ፡ ደፋር ፡ ሆኜ መተረቻ ፡ እንዳልሆን ፡ በሃፍረት ፡ ተከድኜ አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈጦ ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ ጥፍሩን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x) በተዘረጋ ፡ ክንድ ፡ በበረታችም ፡ እጅ በጌታ ፡ መዳኑን ፡ ከሞት ፡ ከሲዖል ፡ እጅ እንደምን ፡ ዘንግቶ ፡ ሰው ፡ ያጉረመርማል ወንድሙን ፡ ለመውገር ፡ እጁን ፡ ይዘረጋል አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈጦ ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ ጥርሱን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x) ስፍራውን ፡ ለቆ ፡ ሲሄድ ፡ ለመጉደፍ ፡ ሲቸኩል ትህትናውን ፡ አውልቆ ፡ ለሞት ፡ ሲንቀለቀል እዪት ፡ ያንን ፡ ዝንጉ ፡ ቃል ፡ ኪዳኑን ፡ ሲያፈርስ በአመጻው ፡ ብዛት ፡ ፍቅርን ፡ ሲያቀዘቅዝ አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈጦ ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ ጥፍሩን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x) አንተን ፡ እየፈራሁ ፡ ቀኑን ፡ ሁሉ ፡ ልኑር ትህትናም ፡ አይራቀኝ ፡ አልነፈግህ ፡ ክብር እጅህ ፡ እንዳይመታኝ ፡ አጉል ፡ ደፋር ፡ ሆኜ መተረቻ ፡ እንዳልሆን ፡ በሃፍረት ፡ ተከድኜ አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈጦ ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ ጥፍሩን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Tesfaye Gabisso

See all 75 songs by Tesfaye Gabisso