Gubae

በአምላክ አምሳል

Bamlak Amsal

ተስፋዬ ጋቢሶ · እግዚአብሔር መንፈስ ነው

Bamlak Amsal is an Amharic mezmur (worship song) by Tesfaye Gabisso, from the album Egziabhier Menfes New.

በአምላክ ፡ አምሳል ፡ ተፈጥሬ ፡ በጐ ፡ ለማድረግ ፡ በፊቱ ስኖር ፡ ሳለሁ ፡ ኃጥያቴ ፡ አድርጐኝ ፡ ነበር ፡ ከንቱ ክቡር ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁ ፡ አምላኬን ፡ ረስቼ እንደሚጠፉ ፡ እንስሶች ፡ መሰልኩ እኔ ፡ ሳልፈልገው ፡ ጌታ ፡ ሊፈልገኝ ፡ ከላይ ፡ መጥቶ ከእርኩሰት ፡ ውስጥ ፡ ነጥቆ ፡ አወጣኝ ፡ በዓለም ፡ ላይ ፡ ተንከራቶ ሸክሜን ፡ ወሰደልኝ ፡ በሥጋዬ ፡ ሞተልኝ የማይቆጠረውን ፡ በደሌን ፡ ፋቀልኝ መድኃኒቴ ፡ ነው ፡ ኢየሱሴ ፡ ጌታዬና ፡ አምላኬ ስለ ፡ መልካሙ ፡ ውለታው ፡ ላመስግነው ፡ ተንበርክኬ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ማዳኑ ፡ ግሩም ፡ ነው ለአምላካዊ ፡ ፍቅሩ ፡ መጨረሻ ፡ የለው በሞት ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ እያለሁ ፡ በድቅድቅ ፡ ጨለማ ኢየሱስ ፡ ብርሃኔ ፡ መጥቶ ፡ አዳነኝ ፡ መሀሪ ፡ ነውና ለፍርድ ፡ የተመደብኩ ፡ ለሲዖል ፡ የታጨሁ የቁጣ ፡ ልጅ ፡ ስሆን ፡ ከፍጥረቴ ቅጣቴን ፡ ውስዶ ፡ ያ ፡ ረድኤቴ (፪x) በአምላክ ፡ አምሳል ፡ ተፈጥሬ ፡ በጐ ፡ ለማድረግ ፡ በፊቱ ስኖር ፡ ሳለሁ ፡ ኃጥያቴ ፡ አድርጐኝ ፡ ነበር ፡ ከንቱ ክቡር ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁ ፡ አምላኬን ፡ ረስቼ እንደሚጠፉ ፡ እንስሶች ፡ መሰልኩ እኔ ፡ ሳልፈልገው ፡ ጌታ ፡ ሊፈልገኝ ፡ ከላይ ፡ መጥቶ ከእርኩሰት ፡ ውስጥ ፡ ነጥቆ ፡ አወጣኝ ፡ በዓለም ፡ ላይ ፡ ተንከራቶ ሸክሜን ፡ ወሰደልኝ ፡ በሥጋዬ ፡ ሞተልኝ የማይቆጠረውን ፡ በደሌን ፡ ፋቀልኝ መድኃኒቴ ፡ ነው ፡ ኢየሱሴ ፡ ጌታዬና ፡ አምላኬ ስለ ፡ መልካሙ ፡ ውለታው ፡ ላመስግነው ፡ ተንበርክኬ ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ማዳኑ ፡ ግሩም ፡ ነው ለአምላካዊ ፡ ፍቅሩ ፡ መጨረሻ ፡ የለው በሞት ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ እያለሁ ፡ በድቅድቅ ፡ ጨለማ ኢየሱስ ፡ ብርሃኔ ፡ መጥቶ ፡ አዳነኝ ፡ መሀሪ ፡ ነውና ለፍርድ ፡ የተመደብኩ ፡ ለሲዖል ፡ የታጨሁ የቁጣ ፡ ልጅ ፡ ስሆን ፡ ከፍጥረቴ ቅጣቴን ፡ ውስዶ ፡ ያ ፡ ረድኤቴ (፪x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Tesfaye Gabisso

See all 75 songs by Tesfaye Gabisso