Gubae

የካሳ ዘመን

Yekasa Zemen

ቴዎድሮስ ታደሰ · የካሳ ዘመን

Yekasa Zemen is an Amharic mezmur (worship song) by Teodros Tadesse, from the album Yekasa Zemen.

"ሰማይ ፡ ምድር ፡ ይስማኝ ፡ ፍጥረት ፡ ያድምጠኝ እግዚአብሔር ፡ ያሰበው ፡ ጸሎቱ ፡ የተሰማ ፡ ያ ፡ ሰው ፡ እኔ ፡ ነኝ እኔ ፡ ነኝ" በቆዘምኩበት ፡ ዘመን ፡ ፈንታ ከፍ ፡ ሊያደርገኝ ፡ ደጉ ፡ ጌታ መከራዬንም ፡ ሊያስረሳኝ ቀኑን ፡ ጠብቆ ፡ መጣልኝ ባለቀስኩበት ፡ ዘመን ፡ ፈንታ ደግሞ ፡ ሊያስቀኝ ፡ ደጉ ፡ ጌታ መከራዬንም ፡ ሊያስረሳኝ ቀኑን ፡ ጠብቆ ፡ መጣልኝ የካሳ ፡ ዘመን ፡ አለ ፡ ከፊቴ (፪x) ልውጣ ፡ ልውረሰው ፡ ወግድ ፡ ጠላቴ ፡ ዞርበል ፡ ጠላቴ የበቀል ፡ ቅባት ፡ ስላረፈብኝ ኪዳንህ ፡ ፈርሷል ፡ ዳግም ፡ ላትገዛኝ (፪x) ወራሽ ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁ ፡ እርስት ፡ እንደሌለው የሃዘን ፡ የለቅሶ ፡ ቤቴን ፡ ልታደርገው ወገን ፡ ዘመድ ፡ ያጣ ፡ ባይተዋር ፡ ብቸኛ ብለህ ፡ ስትጣራ ፡ ጌታ ፡ መጣልኛ በሰው ፡ አቆጣጠር ፡ ቢመስል ፡ የዘገየ እውነተኛ ፡ ዳኛ ፡ መገፋቴን ፡ አየ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁ በጨለማ ፡ ብሄድ ፡ ጌታ ፡ ብርሃኔ ፡ ነው የጠራኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይጥልም ፡ አውቃለሁ እንዳልሰማ ፡ የአንተን ፡ ስብከት ውሸታም ፡ ነህ ፡ የውሸት ፡ አባት ፈጣሪዬን ፡ ለእኔ ፡ ልታማ ብዙ ፡ ሞከርክ ፡ መች ፡ ልታቅማማ እኔስ ፡ የማውቀው ፡ ይሄን ፡ ነው እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነው (እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መልካም) (፬x) በቆዘምኩበት ፡ ዘመን ፡ ፈንታ ከፍ ፡ ሊያደርገኝ ፡ ደጉ ፡ ጌታ መከራዬንም ፡ ሊያስረሳኝ ቀኑን ፡ ጠብቆ ፡ መጣልኝ ባለቀስኩበት ፡ ዘመን ፡ ፈንታ ደግሞ ፡ ሊያስቀኝ ፡ ደጉ ፡ ጌታ መከራዬንም ፡ ሊያስረሳኝ ቀኑን ፡ ጠብቆ ፡ መጣልኝ የካሳ ፡ ዘመን ፡ አለ ፡ ከፊቴ (፪x) ልውጣ ፡ ልውረሰው ፡ ወግድ ፡ ጠላቴ ፡ ዞርበል ፡ ጠላቴ የበቀል ፡ ቅባት ፡ ስላረፈብኝ ኪዳንህ ፡ ፈርሷል ፡ ዳግም ፡ ላትገዛኝ (፪x) ከላይ ፡ አዞልኛል ፡ የሰማይ ፡ አባቴ ሞልቶ ፡ እንዲትረፈረፍ ፡ በበረከት ፡ ቤቴ የሚያስፈልገኝን:ስለሚያውቅልኝ ከእኔ ፡ ይልቅ ፡ ለእኔ ፡ የሚያስብልኝ አምላክ ፡ አለኝና ፡ እጅግ ፡ ባለጠጋ ለምንስ ፡ ልሳቀቅ ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ልሥጋ ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ብወድቅ ፡ እነሳለሁ በጨለማ ፡ ብሄድ ፡ ጌታ ፡ ብርሃኔ ፡ ነው የጠራኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይጥልም ፡ አውቃለሁ እንዳልሰማ ፡ የአንተን ፡ ስብከት ውሸታም ፡ ነህ ፡ የውሸት ፡ አባት ፈጣሪዬን ፡ ለእኔ ፡ ልታማ ብዙ ፡ ሞከርክ ፡ መች ፡ ልታቅማማ እኔስ ፡ የማውቀው ፡ ይሄን ፡ ነው እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መልካም ፡ ነው (እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ መልካም) (፬x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Teodros Tadesse

See all 37 songs by Teodros Tadesse