Gubae

የበረሃው ጓዴ

Ye%27berehaw guade

ኢየሩሳሌም ነጋያ · 3

Ye%27berehaw guade is an Amharic mezmur (worship song) by Eyerusalem Negiya, from the album 3.

ማን ነበረ ከጎኔ ያኔ?  ያልተለየኝ ከአጠገቤ? ሀዘን ሲያቆስለው ልቤን ሳስታውሰው መከራዬን የተወለድኩበትን ቀን  ስረግመው ደጋግሜ። አንዱ ሳያበቃ የኑሮዬ ሲቃ ሲደራረብብኝ ውስጤን ሲደቁሰው እውነት ነበረኝ ወይ? እውነተኛ አፅናኝ የውስጥ ጥልቅ ስሜቴን አውቆ የተረዳኝ ፈራጅ እንጂ አፅናኝ ነበረኝ ወይ? የመሰለውን የተሰማውን ባይ አዝነው ሲያስተክዙኝ መልሰው ሲያቆስሉኝ ብሶቴን ቀስቅሰው አልቃሻ አረጉኝ የበረሀው ጓዴ የጥሻው ዘመዴ ለካስ ወዳጅ አለኝ ባያዩህ ይህ አይኔ ከወንድም አብልጦ በጣም የሚጠጋ ተረድቶ የሚረዳ ስለኔ ያለው ዋጋ። አለሁ ባዬ መከታዬ ኢየሱስ ጌታዬ ልጄ አትፍሪ ተደገፊ ትከሻዬ ሰፊ እያለ ያፅናናኝ ያበረታኝ ክንዴ ከጎኔ የቆመ ያባባለኝ ውዴ እንባዬን ጠራርጎ አፌን በሳቅ ሞላ መከራዬ ሄደ ቀረ ወደ ዃላ። ኢየሱስ(*2) እውነተኛ ወዳጅ ኢየሱስ(*2) ከልብ የሚወዳጅ ኢየሱስ(*2) ታማኝ ባልንጀራ ኢየሱስ(*2) ቀን ሲጥል የማይከዳ ኢየሱስ(*2) ኢየሱስ(*2) ቀን ሲጥል የማይከዳ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Eyerusalem Negiya

See all 26 songs by Eyerusalem Negiya