Gubae

ረግረጉ ደረቀ

Eregregu dereke

ኢየሩሳሌም ነጋያ · 3

Eregregu dereke is an Amharic mezmur (worship song) by Eyerusalem Negiya, from the album 3.

እግዚአብሔር ከኔ ጋር ባይሆንማ ኖሮ የጠላቴ ቁጣ በኔ ላይ በርትቶ በህይወት ሳለሁኝ በዋጠኝ ነበረ ታሪኬን ሊያስቀረው እያለ እንዳልነበረ ለጥርሱ ንክሻ አልተተውኩም እንዳሰበው ክፉ አላገኘኝም ለጥርሱ ንክሻ አልተተውኩም እንዳሰበው ጠላት አላጠፋኝም ጠላቴማ ሊለያየኝ ስንት ጊዜ ሞከረ ሊነጥለኝ ከእውነት ስንት ጊዜ ጣረ ጌታ ጣልቃ እየገባ ምክሩን እያፈረሰ የሸፈተው ልቤን ወደራሱ መለሰ በፀሎቴ አለፍኩት አልልም ያንን ሁሉ ወጀብ በጉልበቴስ መች በተንኩት አስፈሪውን አጀብ በፅናቴ ተወጣሁት አልልም ያን ዳገት አቀበት በብልጠቴስ መች ሾለኩኝ ከዛ ሁሉ ውድቀት ፀጋህ ተትረፍርፎ ምህረትህ በዝቶልኝ የማልችለው ተቻለኝ ከባዱ ቀለለኝ እረግረጉ ደረቀ ጎርባጣውም ቀና የዘመመው ማገሬ እንደገና ፀና ሰባራውን ድልድይ እየገጠመ ጎርፉን እየገደበ ስፍገመገም እጄን በእጁ ይዞ እግሬን አሻገረ በስሙ አለት ላይ አፀናኝና እንዳወራ የሱን ዝና ዜማን እና ቅኔን አስታጠቀኝ ዘምርለታለሁ ገና አዜምለታለሁ ገና እቀኝለታለሁ ገና እኖርለታለሁ ገና አገለግላለሁ ገና

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Eyerusalem Negiya

See all 26 songs by Eyerusalem Negiya