Gubae

ዘላለማዊ

Zelalemawi

እንዳለ ወልደጊዮርጊስ · ዘላለማዊ · 2018

Zelalemawi is an Amharic mezmur (worship song) by Endale Woldegiorgis, from the album Zelalemawi (2018).

የማታረጀው ፡ ማትቀደደው ሀሩር ፡ ሲመጣ ፡ ማትቀየረው ዘላለማዊው ፡ ልብሴ ፡ የኔነቴ: ውበት:ግርማ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ የክብር ፡ ሁሉ ፡ መደምደሚያ ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ [2X] አንተን ፡ ለብሶ ፡ ተጐናፅፎ እራቁቱን ፡ ማንስ ፡ ቀርቶ የለበሰህ ፡ ከበረ ፡ እንጂ መቼ ፡ ቆመ ፡ ውርደት ፡ ደጅ አንተን ፡ ያለ ፡ የታደለ ፡ እራቆቱ ፡ ተሸፈነ [2X] ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ [2X] ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ሚለበስ ፡ ሁሉ የማያዛልቅ ፡ ቅጠል ፡ መሆኑ የተረዳ ፡ ሰው ፡ ሌላውን ፡ አውልቆ አንተን ፡ ሲለብሰህ ፡ አዳኙን ፡ አውቆ የሞትን ፡ ነፋስ ፡ ብርድን ፡ አይፈራ ፡ የዘላለሙን ፡ ለብሶሃልና [2X] ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ [2X] የማታረጀው ፡ ማትቀደደው ሀሩር ፡ ሲመጣ ፡ ማትቀየረው ዘላለማዊው ፡ ልብሴ ፡ የኔነቴ: ውበት ፡ ግርማ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ የክብር ፡ ሁሉ ፡ መደምደሚያ ዘላለማዊ ፡ ልብሴ ፡ ነህ ፡ ውበቴ [2X]

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Endale Woldegiorgis

See all 45 songs by Endale Woldegiorgis