Gubae

ጌታ ልዩ ነው

Geta Leyu New

እንዳለ ወልደጊዮርጊስ · ዘላለማዊ · 2018

Geta Leyu New is an Amharic mezmur (worship song) by Endale Woldegiorgis, from the album Zelalemawi (2018).

ነፍሴ ፡ ወደ ፡ ሕያው አምላክ ፡ ተጠማች [፪X] ልረካህ ፡ ብል ፡ እህህ በቃኝ ፡ ልል ፡ ብል ፡ እህህ አልችልም ፡ ኢየሱስ ፡ ሚጠገብ ፡ እኮ ፡ አይደለም እሱ ልዩ ነው ልዩ [፪x] ጌታ ልዩ ነው ልዩ [፪x] ለታላቅነቱ ፡ ለታላቅነቱ ምስጋናውን ፡ አምጡ [፪x] እፎይ ፡ እረካው ፡ የልቤ ፡ ደርሷል አሁን ፡ ለጌታ ፡ ምለው ፡ ምን ፡ ቀርቷል ብዬ ፡ ደምድሜ ፡ ገና ፡ ስል ፡ ቁጭ ብሶ ፡ ይፈልቃል ፡ የዜማው ፡ ምንጭ ብዬ ፡ ነበረ ፡ እንደዚህ ፡ ብዙ ሚያቆም ፡ አይደለም ፡ የዜማው ፡ ወንዙ ይሄን ፡ ስጨርስ ፡ ምለው ፡ ሌላ ፡ አለኝ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ የሚያዘምረኝ እሱ ልዩ ነው ልዩ [፪x] ጌታ ልዩ ነው ልዩ [፪x] ሌቤ ፡ የተመኘው ፡ ነገሬ ፡ ሳገኘው ፡ ደርሶ የውስጥ ፡ ርካታና ፡ ደስታ ፡ አይሰጥ ፡ ጨርሶ ሁሉንም ፡ ነገር ፡ አይቼ ፡ ስልችት ፡ ሲለኝ ዛሬም ፡ ዘላለም ፡ ማይሰለች ፡ አንድ ፡ ጌታ ፡ አለኝ ከዉሃ ፡ ይልቅ ፡ እኔ ፡ ሚጠማኝ ከምግብ ፡ ይልቅ ፡ እኔ ፡ ሚርበኝ [የውስጤ ናፍቆት፡ ኢየሱስ [፪X] የልቤ ናፍቆት፡ ኢየሱስ] [፪x] እሱ ልዩ ነው ልዩ [፪x] ጌታ ልዩ ነው ልዩ [፪x]

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Endale Woldegiorgis

See all 45 songs by Endale Woldegiorgis