Gubae

ወጥመዱ ተሰበረ

Wetmedu Tesebere

ደረጀ ከበደ · አዳኜ ኢየሱስ · 2010

Wetmedu Tesebere is an Amharic mezmur (worship song) by Dereje Kebede, from the album Adagnie Yesus (2010).

አቤቱ የታለ ጠላታችን በነነ ከዓይናችን ከእጁ ተወሰደ መውጊያው ቀስቱ የታመነበቱ ወጥመዱ ተሰበረ ሆ እኛም አመለጥን ጠላትም ደረቀ እኛም ለመለምን (2x) ጉድጓድ ተቆፍሮ ነበር ለእኛ ቁልቁል እንድንገባ እግዚአብሔር ግን ፈጥኖ ፊት ቀደመ ዲያቢሎስ ሰጠመ ወጥመዱ ተሰበረ ሆ እኛም አመለጥን ጠላትም ደረቀ እኛም ለመለምን (2x) በቁጥቋጦ መሃል ጠላት ጠምዶ ሊጥለን አሳዶ ሌት ከቀን አደባ ዐይኑን ከፍቶ መና ሊቀር ለፍቶ ወጥመዱ ተሰበረ ሆ እኛም አመለጥን ጠላትም ደረቀ እኛም ለመለምን (2x) በሰልፍ ያስጨነቀን ብናኝ ሆነ ኃይሉ ተበተነ እንዳረጀ አንበሳ ዝንብ ወረረው ድንፋታው ተለየው።

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Dereje Kebede

See all 72 songs by Dereje Kebede