ዓለምን እንዳላይ
Alemen Endalay
ደረጀ ከበደ · አዳኜ ኢየሱስ · 2010
Alemen Endalay is an Amharic mezmur (worship song) by Dereje Kebede, from the album Adagnie Yesus (2010).
ግራ ቀኝም አልል በአይኖቼ እወድቃለሁና ሰልችቼ ለውድቀት ካልሆነ በስተቀር ይቅርብኝ ከሰው ሁሉም ነገር ዓይኔን ከሰው አንስቻለሁ አንተኑ ብቻ እጣራለሁ ድል እስክትሰጠኝ እጠብቃለሁ ሁሉም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው ካንተ ማግኘት ጥበብ ነው ጌታ አለኝ ብያለሁኝና በድፍረት ፎክሬያለሁና ስጠራህ ከተፍ በል ረድኤቴ ልኩራብህ እርዳኝ መድኅኒቴ ዓይኔን ከሰው አንስቻለሁ አንተኑ ብቻ እጣራለሁ ድል እስክትሰጠኝ እጠብቃለሁ ሁሉም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው ካንተ ማግኘት ጥበብ ነው በጎነት ከቶ የት ይገኛል ትልቁ ትንሹን ረግጦታል ፍቅርስ ከወዴት ይጋዛል ሰው ሰውን በጥርሱ አላምጦታል ዓይኔን ከሰው አንስቻለሁ አንተኑ ብቻ እጣራለሁ ድል እስክትሰጠኝ እጠብቃለሁ ሁሉም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው ካንተ ማግኘት ጥበብ ነው ጎልጎታ አናተ ላይ ሞተሃል ከጉድጏድ ሽቅብ አርገሃል ቀና ብል አይሃለው አንተን ቸር ወዳጅ የሌለብህ እንከን ዓይኔን ከሰው አንስቻለሁ አንተኑ ብቻ እጣራለሁ ድል እስክትሰጠኝ እጠብቃለሁ ሁሉም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው አንተን ማግኘት ጥበብ ነው ግባ ካዳራሹ ከልቤ አንተ ነህ መኩሪያዬ ጥጋቤ መስቀልህ በፊቴ ተስሎ አፀናኝ ከእንቅፋት ከልሎ ዓይኔን ከሰው አንስቻለሁ አንተኑ ብቻ እጣራለሁ ድል እስክትሰጠኝ እጠብቃለሁ ሁሉም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ነው ካንተ ማግኘት ጥበብ ነው አቤቱ የማትለዋወጥ ደካማን ለጅብ የማትገልጥ አንተ ነህ ኢየሱስ የናዝሬቱ ጥበብ ነው በአንተ መመካቱ


