Gubae

አሃዱ እላለሁኝ

Ahadu Elalehugn

ደረጀ ከበደ · አዳኜ ኢየሱስ · 2010

Ahadu Elalehugn is an Amharic mezmur (worship song) by Dereje Kebede, from the album Adagnie Yesus (2010).

አሃዱ እላለሁ በምስጋና አፌን እክፍታለሁ በምስጋና እርሱ ያሰበልኝ በለጠና የእኔ ከንቱ ሆኖ ቀርቷልና ወጥቼ ወርጄ ብዙ አስቤአለሁ አውጠንጥኛለሁ ልቤ እሰክሚጨነቅ በስጋ ጉዞ ተክለፍልፌአለሁ ኋላ ግን በየሱስ ተሰብስቤያለሁ /፪ ፈቃዱን አውቄ በምስጋና ቃል ስሙን ጠርቼ እውነተኛ ድምፁን ከአንደበቱ ጠርቶኝ ስምቼ እርሱን እጠብቃለሁ ሌላውን ትቼ /፪ በከንቱ ነበረ መደካከሜ ላይ ታች ማለቴ ነገ ዛሬ እንዲሆን በምኞት ሩጫ እጅግ መትጋቴ አሁን ግን ልቀበል ከላይ ካባቴ /፪ እንግዲህ ካገኘሁ አጋዥ ከአርያም ሐሳቤን ጠቅላይ ደቂቃም አታልፍም አይኔን አንስቼ ወደላይ ሳላይ ድል ይላክልኛል ከሩቅ ከሰማይ /፪

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Dereje Kebede

See all 72 songs by Dereje Kebede