Gubae

ሰው ሌላ ሌላ ሲል

Sew Liela Liela Sil

ካሌብ ተስፋዬ · ትንሳኤ አለ · 2009

Sew Liela Liela Sil is an Amharic mezmur (worship song) by Caleb Tesfaye, from the album Tensae Ale (2009).

ዘማሪ ካሌብ ተስፋዬ ርዕስ ሰው ሌላ ሌላ ሲል አልበም ትንሳኤ አለ አለልኝ የምልብህ ትምክህቴ የምመካብህ የድሃ ቀኜ ምርኩዝ ነህ አለኝታ ነህ ታኮራለህ ማንም ባይኖረኝ ዙሪያዬ ማዶ ቢሆንም ጓዳዬ አለሁልህ የሚል ቢጠፋ ጌታ እኮ ነህ የእኔ ተስፋ ሰው ሌላ ሌላ ሲል ሲኮራ በእንጀራው እኔ ግን ከእጅህ ነው ጠግቤ የምበላው (፪x) (ክላሲካል) ከእሳት ይልቅ የበረታ ሰልፌ ኑሮ ጥዋት ማታ ደምህ ከለላ ሆኖኝ እንዳይፈጀኝ ጠብቆኝ ተጠነከክልኝና ባሕሩን ከፈልከውና ተሻገርኩኝ ሄድኩኝ ማዶ ነበር ነገር ሁሉ ከብዶ መች ቀላል ሆነና ያለፍኩት ጐዳና ለመኖር በቃሁኝ በእጅህ ተያዝኩና (፪x) (ክላሲካ) ሳየው ዞሬ ወደ ኋላ ባይኖረኝ የአንተ ከለላ ተረት ሆኜ ቀር ነበረ ምሕረትህ በዛ ጨመረ ከፈተና መውጫ ብሩ መኖር አንተን እየጠሩ አታሳፍር መልስ አለህ ለጭንቅ ቀን ደራስህ ነህ ከጉድጓድ ከወጡ ከሞት ካመለጡ ከዚህ በላይ ደስታ ምን አለና ጌታ (፪x) (ክላሲካል) ከእናት በላይ እናት ብልህ ከአባት በላይ አባት ብልህ አይበቃ ሥም ቢሰጥህ ከዚህ ሁሉ የላክ ነህ ሳልወድህ ስለ ወደድከኝ ሳልመርጥህ ስለ መረጥከኝ ንጉሥ ሆይ እኔም ምሥጋና አለኝ ከነኃጢአቴ ተቀበልከኝ ጉድለቴን የሞላ አንተን የለ ሌላ ሞገስ ማዕረጌ ነህ ወግ ያየሁብህ (፪x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Caleb Tesfaye

See all 27 songs by Caleb Tesfaye