Gubae

ኢየሱስ

Iyesus

ካሌብ ተስፋዬ · ትንሳኤ አለ · 2009

Iyesus is an Amharic mezmur (worship song) by Caleb Tesfaye, from the album Tensae Ale (2009).

በምድር ላይ የገነኑ ሞት ሲመጣ ሲፈተኑ ሊያመልጡ አልቻሉም በቃቸው ስጋ ለባሽ አፈር ናቸው ግን ይሄ ንጉስ መቃብሩን ተሰማለት መፈንቀሉን ወጣ የሙታኑ በኩር የክቡራን ሁሉ ክቡር እየሱስ ጌታ ነው እየሱስ ህያው ነው እየሱስ ጀግና ነው እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ ስሙ ሲጠራ የማይፈራ "እኔ ነኝ" ያለ ተራራ ይናዳል ይሆናል ሜዳ ታይቷል ስንቱን ሰው ሲረዳ ወጀቡም ፀጥ ማዕበልም ፀጥ ካዘዘ እሱ ማን ሊቀመጥ ግርማው ክብሩ የተለየ ገናና ከፍ ብሎ የቆየ እየሱስ ሁሉን ቻይ ነው እየሱስ ሃያል ነው እየሱስ ብርቱ ነው እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ ነፍስ ያስጨነቁ አጋንንቶች ከንቱ ምናምንቴዎች ሲታዘዙ ወዮ እያሉ በእሳት ተገርፈው ይለቃሉ ማን ሰማና ማን አየና? ይህን የመሰለ ጀግና ሰማይ ቢወጣ ምድር ላይ አይን እሱን የመሰለ አያይ እየሱስ ገናና ነው እየሱስ ልዩ ነው እየሱስ ታላቅ ነው እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ ለጥያቄ ሁሉ መልሱ ለበሽታ ሁሉ ፈውሱ አንድ እና አንድ እሱ ብቻ ቁልፍ ነው የሁሉ መፍቻ ደቆሮውን፣ ዲዳውን መሄድ ያልቻለ ሽባውን ኧረ ስንቱን ነፃ አወጣ ቤቱ ድረስ እየመጣ እየሱስ ፈዋሽ ነው እየሱስ ተስፋ ነው እየሱስ አዳኝ ነው እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ፣ እየሱስ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Caleb Tesfaye

See all 27 songs by Caleb Tesfaye