Gubae

የኤማሁስ መንገደኞች

Yeiemahus Mengedegnoch

አገኝሁ ይደግ · ብዙ የሆንክልኝ · 2009

Yeiemahus Mengedegnoch is an Amharic mezmur (worship song) by Agegnehu Yideg, from the album Bezu Yehonkelegn (2009).

የተስፋን ቃል የሰጣችሁ የታመነ ነውና በስፍራችሁ ሆናችሁ ጠብቁት ታገሱና እግዚአብሔር አይጨክንም ያስብላችኋል እርሱ ሰብሯችኋልና እርሱ ይጠግናችኋል አዝ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ ጠውልጋችሁ ዝላችኋል የምትሉትን አታውቁም ስንፍናና ዝንጉነትን ለምን ከእናንተ አታርቁም እግዚአብሔር እረስቶናል እባካችሁን አትበሉ የሚበዣችሁ ኢየሱስ ታማኝ ነው እኮ ለቃሉ አዝ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ ይቤዠናል ብለን ነበረ ተስፋ ያደረግነው ለካስ የናዝሬቱ ኢየሱስ እንደዚህ ዓይነት አምላክ ነው ስለምን እንደዚህ ትናገራላችሁ ጌታችን ከሞት ተነስቶ አሁን እኮ አለ አብሯችሁ አዝ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ስፍራችሁን ለቃችኋል እግዚአብሔር ያላችሁን በሙሉ ዘንግታችኋል የገባላችሁን ተስፋ እናንተ እንኳን ብትረሱ እግዚአብሔር ግን አይረሳም ከሞት ተነስቷል ንጉሡ አዝ የኤማሆስ መንገደኞች የጌታ ደቀ መዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሡ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Agegnehu Yideg

See all 51 songs by Agegnehu Yideg