ክቡር ክቡር
Kebur Kebur
አዲሱ ወርቁ · የመስቀሉ ፍቅር · 2006
Kebur Kebur is an Amharic mezmur (worship song) by Addisu Worku, from the album Yemesqelu Fikir (2006).
ብዙ ሃያላን ነበሩ በአምላኬ ላይ የተኩራሩ ቅዱሱን ሀይል የተገዳደሩ ያ ዝናቸው አምድ ለብሶ ታሪካቸው ተቀልብሶ አለ ጌታ በላያቸው ነግሶ አዝ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (፪x) ሃብታም በሃብቱ ይኮራል ሃያል በኃይሉ ይመካል ስልጣን ያለው ጭቁኑን ይንቃል ነገር ግን ቅኑ ፈራጅ ከላይ ተቀምጧል ከዙፋን ላይ ክንደ ብርቱ ጻድቁ ኤልሻዳይ አዝ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (፪x) የመከራ ወንዝ ሲሞላ የጐበዝ ወኔ ሲላላ ማነው ጽኑ ከአምላካችን ሌላ የፈረሰ ሕይወት ጠጋኝ ሁሉ ሲክድ ቀሪ ታማኝ እግዚአብሔር ነው ለዘለዓለም ታማኝ አዝ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (፪x) ለዛለው ምርኩዝ ደጋፊ የደከመን አሳራፊ ሁሉን ታጋሽ ፍፁም ልበ ሰፊ የመሸበት አሳዳሪ ለተጠቃ ተቆርቋሪ እግዚአብሔር ነው ለዘለዓለም ነዋሪ አዝ ክቡር ክቡር ሃያል ክቡር ለዘለዓለም የምትኖር አምላካችን እግዚአብሔር (፫x)


