Gubae

ከኖሩማ

Kenoruma

ዮሴፍ ካሳ · ዘመቻው

Kenoruma is an Amharic mezmur (worship song) by Yosef Kassa, from the album Zemetaw.

ንፋሱ ፡ ነፈሰና ፡ አለፈ ወጀቡም ፡ ጸጥ ፡ አለ ፡ አለፈ መንገዴን ፡ ዞር ፡ ብዬ ፡ ሳየው ይህ ፡ ሁሉ ፡ ለመልካም ፡ የሆነው ስላለ ፡ ጌታ ፡ አጠገቤ ስላለ ፡ አባ ፡ አጠገቤ ከኖሩማ ፡ ኑሮ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ በችግር ፡ ቢሆን ፡ በመከራ ከተያዘም ፡ እጄ ፡ በአንተ ፡ እጅ ሕይወቴ ፡ ሰላም ፡ ነው ፡ የሚመች ስሄድ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ በሕይወት ፡ መንገድ ምንም ፡ ነገር ፡ አይሆን ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ ፈቃድ አያስጨንቀኝም ፡ ነገ ፡ የሚሆነው የነፍሴ ፡ ፍጻሜ ፡ በእጅህ ፡ ነው የእኔ ፡ ነገር ፡ ሰው ፡ የማይዘጋው ፡ ሰው ፡ የማይከፍተው ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው የእኔ ፡ ነገር ፡ መጀመሪያዬ ፡ መጨረሻዬ በእርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ ከኖሩማ ፡ ኑሮ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ በችግር ፡ ቢሆን ፡ በመከራ ከተያዘም ፡ እጄ ፡ በአንተ ፡ እጅ ሕይወቴ ፡ ሰላም ፡ ነው ፡ የሚመች ሲጸልይ ፡ ዳንኤል ፡ አንተን ፡ ስለጠራ ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ ከተቱት ፡ በአንበሳ ፡ እንዲበላ ይንከባከቡታል ፡ እንኳን ፡ ሊበሉት ችግር ፡ ይቀየራል ፡ በምቾት የእኔ ፡ ነገር ፡ ሰው ፡ የማይዘጋው ፡ ሰው ፡ የማይከፍተው ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው የእኔ ፡ ነገር ፡ መጀመሪያዬ ፡ መጨረሻዬ በእርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ ቆይ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ከአንተ ፡ የራቀ ፡ የተሰወረብህ እኮ ፡ ምን ፡ አለ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ሁሉን ፡ የምታውቅ ቆይ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ድንገት ፡ ተገልጦ ፡ የሚያስደነግጥህ እኮ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ሰማይ ፡ ምድሩን ፡ ሁሉን ፡ በእጅህ ፡ ይዘህ መላ ፡ ሕይወቴ ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ እድሜ ፡ ዘመኔ ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ነገዬም ፡ ቢሆን ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ እስትንፋሴ ፡ እንኳን ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Yosef Kassa

See all 37 songs by Yosef Kassa