Gubae

እጄን አነሳሁ

Ejien Anesaw

ዮሴፍ ካሳ · ዘመቻው

Ejien Anesaw is an Amharic mezmur (worship song) by Yosef Kassa, from the album Zemetaw.

የልቤን ፡ ማዋየው ፡ የውስጤን ፡ ሚስጥረኛዬ ባዝንም ፡ ብከፋም ፡ ማይለየኝ ፡ መጽናኛዬ ነፍሴ ፡ ትረካለች ፡ በአንደበቱ ፡ ቃል ፡ በምክሩ የመኖሬ ፡ ትርጉም ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሚስጥሩ ወደ ፡ አባቴ ፡ ልቅረብ ፡ እንጂ የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ውጪ ወደ ፡ አባቴ ፡ ልቅረብ ፡ እንጂ የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ውጪ እጄን ፡ አነሳሁ ፡ ወደ ፡ ላይ ወደ ፡ ሚሰማኝ ፡ ወደሚያይ ጩኸቴን ፡ ሰምቶ ፡ ይመልሳል እንባዬን ፡ ከዓይኔ ፡ ያብሳል አባትዬ ፡ አባትዬ ፡ አባብዬ ከእስትንፋሴ ፡ ይልቅ ፡ ይቀርበኛል ፡ አይርቀኝም የፍቅር ፡ ቃል ፡ ኪዳን ፡ ገብቶልኛል ፡ አይተወኝም እንዳወራው ፡ ድፍረት ፡ ይሰጠኛል ፡ የፍቅር ፡ ዓይኖቹ ልቤ ፡ ተፈወሰ ፡ ሲዳስሰኝ ፡ በመልካም ፡ እጆቹ መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ መልካም ፡ ነህ መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ መልካም ፡ ነህ የልቤን ፡ ማዋየው ፡ የውስጤን ፡ ሚስጥረኛዬ ባዝንም ፡ ብከፋም ፡ ማይለየኝ ፡ መጽናኛዬ ነፍሴ ፡ ትረካለች ፡ በአንደበቱ ፡ ቃል ፡ በምክሩ የመኖሬ ፡ ትርጉም ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሚስጥሩ ወደ ፡ አባቴ ፡ ልቅረብ ፡ እንጂ የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ውጪ ወደ ፡ አባቴ ፡ ልቅረብ ፡ እንጂ የሚረዳኝ ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ውጪ እጄን ፡ አነሳሁ ፡ ወደ ፡ ላይ ወደ ፡ ሚሰማኝ ፡ ወደሚያይ ጩኸቴን ፡ ሰምቶ ፡ ይመልሳል እንባዬን ፡ ከዓይኔ ፡ ያብሳል አባትዬ ፡ አባትዬ ፡ አባብዬ ትዋሽ ፡ ዘንድ ፡ እንደሰው ፡ አይደለህ ፡ እውነተኛ ፡ ነህ የተናገርከውን ፡ ታደርጋለህ ፡ ትፈጽማለህ ቢታመኑህ ፡ ታማኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ወረት ፡ የሌለህ ከአጠገቤ ፡ ሁሌ ፡ ማትለየኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ መልካም ፡ ነህ መልካም ፡ ነህ ፡ መልካም ፡ መልካም ፡ ነህ ትልቅነትህ ፡ እየገረመኝ አጠገቤ ፡ ነህ ፡ ይሄም ፡ ሲደንቀኝ ዘልቀህ ፡ ውስጤ ፡ ገብተሃል መኖሪያህን ፡ አድርገሃል የእኔ ፡ ሆነሃል

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Yosef Kassa

See all 37 songs by Yosef Kassa