Gubae

ልባርክህ

Lebarkeh

ትዕግስት አለሙ · ማራናታ

Lebarkeh is an Amharic mezmur (worship song) by Tigist Alemu, from the album Maranatha.

ባከብርህ ፡ ባመልክህ ፡ ባመሰግንህ ተባረክ ፡ ተወደስ ፡ ክበር ፡ እያልኩህ መቼ ፡ ይበቃኛል ፡ አንተን ፡ ሊገልጽህ ለእኔ ፡ ታደረከው ፡ ጌታ ፡ እየበዛብኝ በተከፋሁ ፡ ጊዜ ፡ ልቤ ፡ ሃዘን ፡ ሲውጠኝ አንተ ፡ ብቻ ፡ ለእኔ ፡ ፈጥነህ ፡ ደረስክልኝ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ሆነህ ፡ ነፍሴን ፡ እያጽናናህ ያንን ፡ ጨለማዬን ፡ በብርሃንህ ፡ አበራህ ስለዚህ ፡ ጌታዬ ፡ ወዳጄና ፡ አባቴ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ፡ ይህን ፡ ፍቅር ፡ ትቼ (፪x) በፊትህ ፡ ስበድል ፡ በአመጼ ፡ ስትቀጣኝ በበደሌ ፡ አዝኜ ፡ ፊትህን ፡ ላይ ፡ ስመኝ አይተህ ፡ አዘንክልኝ ፡ በንስሃ ፡ ሞልተህ ጽድቅን ፡ አወጣሃት ፡ ጠላቴን ፡ ረግጠህ ድካሜ ፡ ቢበዛ ፡ ጉድለቴ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሙላቴ እንዲሁ ፡ በፀጋህ ፡ ቆሜያለሁ ሥምህን ፡ በዜማ ፡ አከብራለሁ (፪x) ይገርመኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ ይደንቀኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ (፪x) የዳንኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የቆምኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የሚያጽናናኝ ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የሚያስኬደኝ ፡ ሃሌሉያ ድካሜ ፡ ቢበዛ ፡ ጉድለቴ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሙላቴ እንዲሁ ፡ በፀጋህ ፡ ቆሜያለሁ ሥምህን ፡ በዜማ ፡ አከብራለሁ (፪x) ይገርመኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ ይደንቀኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ (፪x) የዳንኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የቆምኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የሚያጽናናኝ ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የሚያስኬደኝ ፡ ሃሌሉያ ባከብርህ ፡ ባመልክህ ፡ ባመሰግንህ ተባረክ ፡ ተወደስ ፡ ክበር ፡ እያልኩህ መቼ ፡ ይበቃኛል ፡ አንተን ፡ ሊገልጽህ ለእኔ ፡ ታደረከው ፡ ጌታ ፡ እየበዛብኝ በተከፋሁ ፡ ጊዜ ፡ ልቤ ፡ ሃዘን ፡ ሲውጠኝ አንተ ፡ ብቻ ፡ ለእኔ ፡ ፈጥነህ ፡ ደረስክልኝ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ሆነህ ፡ ነፍሴን ፡ እያጽናናህ ያንን ፡ ጨለማዬን ፡ በብርሃንህ ፡ አበራህ ስለዚህ ፡ ጌታዬ ፡ ወዳጄና ፡ አባቴ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ፡ ይህን ፡ ፍቅር ፡ ትቼ (፪x) በፊትህ ፡ ስበድል ፡ በአመጼ ፡ ስትቀጣኝ በበደሌ ፡ አዝኜ ፡ ፊትህን ፡ ላይ ፡ ስመኝ አይተህ ፡ አዘንክልኝ ፡ በንስሃ ፡ ሞልተህ ጽድቅን ፡ አወጣሃት ፡ ጠላቴን ፡ ረግጠህ ድካሜ ፡ ቢበዛ ፡ ጉድለቴ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሙላቴ እንዲሁ ፡ በፀጋህ ፡ ቆሜያለሁ ሥምህን ፡ በዜማ ፡ አከብራለሁ (፪x) ይገርመኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ ይደንቀኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ (፪x) የዳንኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የቆምኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የሚያጽናናኝ ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የሚያስኬደኝ ፡ ሃሌሉያ ድካሜ ፡ ቢበዛ ፡ ጉድለቴ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሙላቴ እንዲሁ ፡ በፀጋህ ፡ ቆሜያለሁ ሥምህን ፡ በዜማ ፡ አከብራለሁ (፪x) ይገርመኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ ይደንቀኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ (፪x) የዳንኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የቆምኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የሚያጽናናኝ ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የሚያስኬደኝ ፡ ሃሌሉያ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Tigist Alemu

See all 12 songs by Tigist Alemu