Gubae

የናዝሬቱ ኢየሱስ

Yenazretu Eyesus

ተስፋዬ ጋቢሶ · የናዝሬቱ ኢየሱስ

Yenazretu Eyesus is an Amharic mezmur (worship song) by Tesfaye Gabisso, from the album Yenazretu Eyesus.

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ርዕስ ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ አልበም ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ጊዜው ፡ ትዝ ፡ ይለናል ፡ የተጠራንበት ትዳሩን ፡ ሊያሸንፍ ፡ ሁሉም ፡ በያለበት ሲወጣና ፡ ሲወርድ ፡ አግኝተህ ፡ ስትጠራው አልማረክ ፡ ብሎ "እምቢ" ያለ ፡ ማነው አዝ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ያለኸው የሚናወጠውን ፡ ወጀብ ፡ በሥልጣንህ ፡ ያዘዝከው ሥምህ ፡ አይጠገብም ፡ ደግመን ፡ ብንወድሰው ደንቆሮዎች ፡ የነበርን ፡ መልካም ፡ ዜና ፡ ሰማን ከብርና ፡ ከወርቅ ፡ መብለጥህን ፡ ተረዳን ሙታን ፡ ስታስነሳ ፡ እውር ፡ ስታበራ ዓይናችን ፡ አይቶሃል ፡ ድንቅ ፡ ሥራ ፡ ስትሰራ አዝ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ያለኸው ፡ የሚናወጠውን ወጀብ ፡ በሥልጣንህ ፡ ያዘዝከው ሥምህ ፡ አይጠገብም ፡ ደግመን ፡ ብንወድሰው ከአንተ ፡ ጋር ፡ ስንጓዝ ፡ በዓለም ፡ ማዕበል ውስጥ ነፋሱን ፡ ገሰጽከው ፡ እኛ ፡ እንዳንሰምጥ ድምፅህ ፡ አይዘነጋም ፡ ያ ፡ የሚያጽናናው ፍቅርህ ፡ እንደ ፡ ጠል ፡ ነው ፡ ለጠወለገ ሰው አዝ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ያለኸው የሚናወጠውን ፡ ወጀብ ፡ በሥልጣንህ ፡ ያዘዝከው ሥምህ ፡ አይጠገብም ፡ ደግመን ፡ ብንወድሰው

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Tesfaye Gabisso

See all 75 songs by Tesfaye Gabisso