Gubae

ነፍሴ ወደ አምላኳ

Nefsie Wede Amlakua

ተስፋዬ ጋቢሶ · የናዝሬቱ ኢየሱስ

Nefsie Wede Amlakua is an Amharic mezmur (worship song) by Tesfaye Gabisso, from the album Yenazretu Eyesus.

ዘማሪ ፡ ተስፋዬ ጋቢሶ ርዕስ ፡ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ አልበም ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ አዝ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ብዬ ፡ ስራዬን ፡ ልጨርስ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ሌት ፡ ተቀን ፡ ልስራና ፡ ሥራዬን ፡ ልጨርስ ሲተጉ ፡ የሚያገኛቸው ፡ ሲመጣ ፡ ጌታቸው በመክሊታቸው ፡ የሰሩ ፡ ምሥጋና ፡ አላቸው አገልግሎቱን ፡ ያልናቀ ፡ በጥቂቱ ፡ ታምኖ ብድራቱን ፡ ይቀበላል ፡ ሥራው ፡ ተፈትኖ አዝ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ብዬ ፡ ስራዬን ፡ ልጨርስ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ሌት ፡ ተቀን ፡ ልስራና ፡ ሥራዬን ፡ ልጨርስ አደራው ፡ ከቶ ፡ የማይገዳቸው ፡ ቸልተኞች የጌታቸውን ፡ መመለስ ፡ የረሱ ፡ ዝንጉዎች ዕድላቸው ፡ ለቅሶ ፡ ነውና ፡ ዋይታ ፡ እንዳይጠብቀኝ መንፈስህ ፡ ዘወትር ፡ ያንቃኝ ፡ ለክብርህ ፡ አቁመኝ አዝ ነፍሴ ፡ ወደ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ብዬ ፡ ስራዬን ፡ ልጨርስ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ሌት ፡ ተቀን ፡ ልስራና ፡ ሥራዬን ፡ ልጨርስ ጥቂት ፡ ታይቶ ፡ ኋላ ፡ እንደሚጠፋ ፡ እንፋሎት እንደ ፡ ሆነ ፡ መች ፡ አጣሁት ፡ ከቶ ፡ የእኔ ፡ ሕይወት እንግዲያው ፡ ታከተኝ ፡ ሳልል ፡ ልሩጥ ፡ ለጌታዬ የሰነፍ ፡ ሰው ፡ ሞት ፡ እንዳልሞት ፡ ልፅና ፡ በዓላማዬ አዝ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ብዬ ፡ ስራዬን ፡ ልጨርስ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ሌት ፡ ተቀን ፡ ልስራና ፡ ስራዬን ፡ ልጨርስ መልካሙን ፡ ገድል ፡ ተጋድያለሁ ፡ አበቃሁኝ ኃይማኖትን ፡ ጠብቄያለሁ ፡ ሩጫውን ፡ ጨረስኩኝ እንደ ፡ ጳውሎስ ፡ ለማለት ፡ ተፈፀመ ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ምሥጋናዬንም ፡ እንዳቀርብ ፡ ለሠራዊት ፡ ንጉሥ አዝ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ብዬ ፡ ስራዬን ፡ ልጨርስ ነፍሴ ፡ ወደ ፡ አምላኳ ሥጋም ፡ ወደ ፡ አፈሩ ፡ ሳይመለስ ሌት ፡ ተቀን ፡ ልስራና ፡ ሥራዬን ፡ ልጨርስ

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Tesfaye Gabisso

See all 75 songs by Tesfaye Gabisso