Gubae

ባለውለታዬ

Balewuletayie

ተፈራ ነጋሽ · አልመለስም

Balewuletayie is an Amharic mezmur (worship song) by Tefera Negash, from the album Alemelesem.

እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አድነኸኛል አመልክሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤዛ ፡ ሆነኸኛል አመሰግናለሁ ፡ ጌታ ፡ ታድገኸኛል አከብርሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ አድርገኸኛል ላመስግንህ ፡ ጠዋትና ፡ ማታ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ ላመስግንህ ፡ ጠዋትና ፡ ማታ ይሄ ፡ ብቻ ፡ አይበቃህም ፡ ጌታ ከሞት ፡ መንደር ፡ በምህረትህ ፡ በቸርነትህ ፡ አውጥተህ ጨለማውን ፡ አስወግደህ ፡ ለዚህ ፡ ክብር ፡ ያበቃኸኝ ሳትሰለች ፡ እያባበልክ ፡ ኃጢአት ፡ በደሌን ፡ ታግሰህ ሰው ፡ አረግከኝ ፡ አተረፍከኝ ፡ ነፍሴን ፡ ከጥፋት ፡ መልሰህ አዝ፦ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ባለውለታዬ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ዋሴ ፡ ጠበቃዬ (፪x) ያለ ፡ እረኛ ፡ ስቅበዘበዝ ፡ በዓለም ፡ ወጥመድ ፡ ተይዤ ፈጣሪዬን ፡ ስበድል ፡ ሳሳዝን ፡ በክፉ ፡ ደንዝዤ እራራህልኝ ፡ ደረስክልኝ ፡ ጸያፍ ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው ልጅ ፡ ተባልኩኝ ፡ ክብር ፡ አገኘሁ ፡ ስሜን ፡ በደም ፡ ቀለም ፡ ጻፍከው አዝ፦ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ባለውለታዬ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ዋሴ ፡ ጠበቃዬ (፪x) እወድሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አድነኸኛል አመልክሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤዛ ፡ ሆነኸኛል አመሰግናለሁ ፡ ጌታ ፡ ታድገኸኛል አከብርሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ አድርገኸኛል ላመስግንህ ፡ ጠዋትና ፡ ማታ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ይገባሃል ፡ ጌታ ላመስግንህ ፡ ጠዋትና ፡ ማታ ይሄ ፡ ብቻ ፡ አይበቃህም ፡ ጌታ ከሞት ፡ መንደር ፡ በምህረትህ ፡ በቸርነትህ ፡ አውጥተህ ጨለማውን ፡ አስወግደህ ፡ ለዚህ ፡ ክብር ፡ ያበቃኸኝ ሳትሰለች ፡ እያባበልክ ፡ ኃጢአት ፡ በደሌን ፡ ታግሰህ ሰው ፡ አረግከኝ ፡ አተረፍከኝ ፡ ነፍሴን ፡ ከጥፋት ፡ መልሰህ አዝ፦ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ባለውለታዬ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ዋሴ ፡ ጠበቃዬ (፪x) ያለ ፡ እረኛ ፡ ስቅበዘበዝ ፡ በዓለም ፡ ወጥመድ ፡ ተይዤ ፈጣሪዬን ፡ ስበድል ፡ ሳሳዝን ፡ በክፉ ፡ ደንዝዤ እራራህልኝ ፡ ደረስክልኝ ፡ ጸያፍ ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው ልጅ ፡ ተባልኩኝ ፡ ክብር ፡ አገኘሁ ፡ ስሜን ፡ በደም ፡ ቀለም ፡ ጻፍከው አዝ፦ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ባለውለታዬ ባለውለታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ዋሴ ፡ ጠበቃዬ (፪x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Tefera Negash

See all 13 songs by Tefera Negash