Gubae

እግዚአብሔር ለእኔ ልዩ ነው

Egziabhier Lenie Leyu New

መስፍን ጉቱ · ተሻገር ያለው · 2004

Egziabhier Lenie Leyu New is an Amharic mezmur (worship song) by Mesfin Gutu, from the album Teshager Yalew (2004).

በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ያለው እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x) ሰማያትን ፡ በሃይሉ ፡ ያጸና በምክሩም ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ እሱ ፡ ገናና እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ ለዘላለም (፪x) አዝ፦በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ያለው እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፫x) እስረኛውን ፡ የፈታ ፡ ያከበረ ምስኪኑን ፡ ሰው ፡ በከፍታ ፡ ላይ ፡ ያኖረ የባርነትን ፡ በትር ፡ የሰበረው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) አዝ፦በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ያለው እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፫x) እግዚአብሔር ፡ በተቀደሰ ፡ መቅደሱ ፡ አለ ጨለማውን ፡ የለየ ፡ ቀኑን ፡ ብርሃን ፡ ይሁን ፡ ያለ ዙፋኑ ፡ በሰማይ ፡ ነው ፡ በሰማይ ፡ ነው ፡ ኦሃሃሃ እንደ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው (ያለ ፡ ማነው) (፬x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Mesfin Gutu

See all 57 songs by Mesfin Gutu