Gubae

ቅዱስ ቅዱስ

Qedus Qedus

ምህረት ኢተፋ · ባለግርማ · 2002

Qedus Qedus is an Amharic mezmur (worship song) by Meheret Etefa, from the album Balegirma (2002).

ቅዱስ ቅዱስ በክብር ያለኸው ዙፋንህ ከጥንት እስከ ዘላለም ነው ክብር ሞገስ ሁልጊዜም አብሮህ ነው ሀሌ ሀሌሉያ እኔ አመልክሀለው ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ እያሉህ ኪሩቤል ሱራፌል እንደሚያመልኩህ መላዕክት በአንድነት እንደሚሰግዱልህ እኔም አመልክሀለው ይኸው በፊትህ(፪*) ቅዱስ ቅዱስ በክብር ያለኸው ዙፋንህ ከጥንት እስከ ዘላለም ነው ክብር ሞገስ ሁልጊዜም አብሮህ ነው ሀሌ ሀሌሉያ እኔ አመልክሀለው የምድርን ውሆች በእፍኝህ ሰፍረሀል የአለምን ተራሮች በሀይልህ አፅንተሀል ሽማግሌዎች ወድቀው ፊትህ ይሰግዱልሀል አቤቱ አምላክ ሆይ ማንስ ይመስልሀል(፪*) ቅዱስ ቅዱስ በክብር ያለኸው ዙፋንህ ከጥንት እስከ ዘላለም ነው ክብር ሞገስ ሁልጊዜም አብሮህ ነው ሀሌ ሀሌሉያ እኔ አመልክሀለው ቅዱስ ቅዱስ ብለው ሲዘምሩልህ ጳውሎስ እና ሲላስ ከልብ ሲያመልኩህ የወህኒውን መሰረተ አናወጠ ሀይልህ በአምልኮ ውስጥ መጣ ታላቁ ክብርህ(፪*) ቅዱስ ቅዱስ በክብር ያለኸው ዙፋንህ ከጥንት እስከ ዘላለም ነው ክብር ሞገስ ሁልጊዜም አብሮህ ነው ሀሌ ሀሌሉያ እኔ አመልክሀለው አእዋፍ ለእኛ የማይገባን ድምፃቸው ከትንሽ ጀምሮ ሁሉም በየቋንቋው ክበር ይሉሀል ያመሰግኑሀል እውነት ነው ጌታ ሆይ ክብር ይገባሀል(፪*) ቅዱስ ቅዱስ በክብር ያለኸው ዙፋንህ ከጥንት እስከ ዘላለም ነው ክብር ሞገስ ሁልጊዜም አብሮህ ነው ሀሌ ሀሌሉያ እኔ አመልክሀለው

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Meheret Etefa

See all 21 songs by Meheret Etefa