Gubae

ለእኔ ክብሬ

Lenie Kebrie

ዳንኤል አምደሚካኤል · የሰው እጅ የሌለበት · 2013

Lenie Kebrie is an Amharic mezmur (worship song) by Daniel Amdemichael, from the album Yesew Ej Yelielebet (2013).

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ውበት ፡ ሞገስ ፡ ዘውድ ፡ አክሊሌ (፪x) ከቶ ፡ የማይርቅ ፡ በፍፁም ፡ ከአጠገቤ ሚራራልኝ ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ ጥጋቤ አይጓደል ፡ በፍፁም ፡ ምሥጋናዉ ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታው በቅዱሳን ፡ ጉባኤ ፡ ህብረት ፡ መሃል ሊመሰገን ፡ ሊከብር ፡ ይገባዋል መልካም ፡ መዓዛ ፡ ሆኖ ፡ ያርግ ፡ መሥዋዕቴ ለወደደኝ ፡ አፍቃሪ ፡ መድሃኒቴ ይድመቅ ፡ ጭብጨባው ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታውም ፡ ይሰማ ምሥጋና ፡ በአሪያም ፡ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ነውና (፪x) የአገኘሁት ፡ ደህንነት ፡ ለመንፈሴ ዳግም ፡ ልደት ፡ በደሙ ፡ መቀደሴ የአምላክ ፡ መንግሥት ፡ ወራሽ ፡ አድርጐኛል ባመሰግን ፡ ብዘምር ፡ ያንስበታል ሆ ፡ ትበል ፡ ዛሬ ፡ ነፍሴ ታምጣ ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ውዳሴ ፡ ለንጉሡ ጌታ ፡ ድንቅ ፡ ነውና (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ውበት ፡ ሞገስ ፡ ዘውድ ፡ አክሊሌ (፪x) ከቶ ፡ የማይርቅ ፡ በፍፁም ፡ ከአጠገቤ ሚራራልኝ ፡ ክብሬ ፡ ነው ፡ ጥጋቤ አይጓደል ፡ በፍፁም ፡ ምሥጋናዉ ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታው ይዘምራል ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ክብሬ ፡ እያለ በአምላኩ ፡ ሰው ፡ መሆኑን ፡ ያስተዋለ ሕይወት ፡ የለውም ፡ ከጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሌላ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ክርስቶስ ፡ የእርሱ ፡ ተድላ ይድመቅ ፡ ጭብጨባው ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታውም ፡ ይሰማ ምሥጋና ፡ በአሪያም ፡ ክብር ፡ ለእርሱ ፡ ነውና (፪x)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Daniel Amdemichael

See all 64 songs by Daniel Amdemichael