Gubae

ኢየሱስ ለእኔም ጌታ ነው

Eyesus Leniem Gieta New

ብዙ ሙሉጌታ · ከአምላካችን በቀር ማነው አምላክ

Eyesus Leniem Gieta New is an Amharic mezmur (worship song) by Bezu Mulugeta, from the album Kamlakachen Beqer Manew Amlak.

እግዚአብሔር ሆይ አመሰግናለሁ ልጅህን ባትሰጠኝ ኖሮ እንዴት እሆናለሁ? ፈቅደህ ስትልከው ወደዚህ ምድር አስበህ አይደለም ወይ እኔ እንድድን። እግዚአብሔር ሆይ ፍቅርህ ይገርመኛል ከስጦታ በላይ ልጅህን ሰጥተኸናል፥ ጊዜው ሰሆነ የመከፈቻው በር ተከፈተ ቃል ስላዘዘው። ያሳፈረኝ ችግር ሲርቅ ለምጼ ሁሉ ከእኔ ሲለቅ ከሰው እኩል እኔም ስሆን ዝም ማለት አቅቶኛል ኢየሱስ ለእኔም ደርሶልኛል። ኢየሱስ ለእኔም ጌታ ነህ(3) ምን እልሃለው? ለሰራኸው ስራ ክብር እሰጥሃለው ክብሬን ጥዬልህ ፊት እሰግዳለው። ሀጥያት (?) የጠፈረኝ ሽባ አድርጎ ያስቀመጠኝ ዛሬስ ጌታ አስቦኛል ድንቅ አምላክ ነው ፈውሶኛል ንጹህ ነሽ ብሎ አቁሞኛል። ጊዜው ሰሆነ የመከፈቻው በር ተከፈተ ቃል ስላዘዘው። እግዚአብሔር ሆይ ፍቅርህ ይገርመኛል ከስጦታ በላይ ልጅህን ሰጥተኸናል። ስኖር ሳለው በጨለማ እየለመንኩ በከተማው ማረኝ ብዬ ስማጸነው ምሕረቱ መቼ ያልቅና አኔም አየሁ እንደሌላ። ኢየሱስ ለእኔም ጌታ ነህ(3) ምን እልሃለው? ለሰራኸው ስራ ክብር እሰጥሃለው ክብሬን ጥዬልህ ፊት እሰግዳለው። እግዚአብሔር ሆይ አመሰግናለሁ ልጅህን ባትሰጠኝ ኖሮ እንዴት እሆናለሁ? ፈቅደህ ስትልከው ወደዚህ ምድር አስበህ አይደለም ወይ እኔ እንድድን። እግዚአብሔር ሆይ ፍቅርህ ይገርመኛል ከስጦታ በላይ ልጅህን ሰጥተኸናል፥ ጊዜው ሰሆነ የመከፈቻው በር ተከፈተ ቃል ስላዘዘው።

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Bezu Mulugeta

See all 15 songs by Bezu Mulugeta