Gubae

አማላጄ

Amalaje

በረከት ተስፋዬ · መምህሩ · 2015

Amalaje is an Amharic mezmur (worship song) by Bereket Tesfaye, from the album Memheru (2015).

የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው (2X) አማላጄ ነው የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው (2X) አማላጄ ነው የሰው ዘር ሁሉ ያዳም ስህተት ይዞት ወደቀ ወደ ጥፋት (2X) ማንም እንዳይድን ይሄን ቢረዳ ሊከፍለው መጣ ለኃጢያት ዕዳ አወይ ለእኔ ዕዳ የኃጢያት ደሞዝ ነውና ሞት ሞቴን ሞተልኝ ሰጠኝ ሂወት (2X) ኃጢያት ተሻረ ከእኔ ላይ በፈሰሰልኝ ጎልጎታ ላይ ቀራኒዮ ላይ በገዛ ደሙ እርቅ አወረደ የጠፋሁትን ስለወደደ ኃጥዕ ተብዬ ስም ለወጣልኝ በደሙ አንፅቶ ፃድቅ አስባለኝ ከደጉ አባቴ አሁን ታረኩ በቅዱስ ደሙ ስለታጠብኩ ሌላ አማላጅ ሳያስፈልገኝ በቀኙ ሆንኩ ደሙ አቀረበኝ የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው (2X) አማላጄ ነው የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው (2X) አማላጄ ነው የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ የማን ፀሎት ነው የሚያስታርቀኝ የኢየሱስ ደም ያላነፃኝ የማን ፀሎት ነው የሚያነፃኝ የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ የማን ምልጃ ነው የሚያስታርቀኝ የኢየሱስ ደም ያላጠበኝ የማን ምልጃ ነው የሚያጥበኝ ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ ስለ ኃጢያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ (2x) የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው (2X) አማላጄ ነው የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው (2X) አማላጄ ነው ለሆንኩት ለኔ ለሞት ፍርደኛ በአብ ቀኛ ያለው አንዱ ብቸኛ ስለበደሌ እሱ ነው ዋሴ የሚቆምልኝ ልክ እንደ ራሴ መሰላል ያየው ያዕቆብ በህልሙ መካከለኛ ነው ክቡር ደሙ ሰማይ ከእኔ ጋር ዕርቅ ያደረገው በማንም አይደል በኢየሱስ ደም ነው ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ ስለ ኃጢያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ (2x) የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው (2X) አማላጄ ነው የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው (2X) አማላጄ ነው

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Bereket Tesfaye

See all 41 songs by Bereket Tesfaye