Gubae

በስግደት

Besigdet

አዜብ ኃይሉ · በመጀመሪያ እግዚአብሔር · 2017

Besigdet is an Amharic mezmur (worship song) by Azeb Hailu, from the album Bemejemberiya Egziabhier (2017).

በስግደት ፡ በአምልኮ ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና ፡ በዕውነት ፡ በመንፈስ ፡ ፊትህ ፡ ልምጣና ፡ ላምልክህ ፡ እንደገና (፫) እንደወራጅ ፡ ዉሃ ፡ ልክ ፡ እንደጅረቱ አይቋረጥብህ ፡ አምልኮዬ ፡ ፊቱ ይፍሰስ ፡ በማለዳው ፡ ይፍሰስ ፡ በሌሊቱ መሳይ ፡ ስለሌለው ፡ ጌታ ፡ ጌትነቱ (፪) ላምልከው ፡ በአምልኮዬ ፡ ላክብረው ፡ በዝማሬዬ ላግንነው ፡ በዕልልታዬ ፡ ላድምቀው ፡ በጭብጨባዬ ይገባዋል ፡ እና ፡ ጌታዬ (፬) የመውደዴን ፡ ልኩን ፡ የፍቅሬን ፡ መግልጫ ካለኝ ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ የምሰጠው ፡ ብልጫ ለሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ለነፍሴ ፡ ንጉሥ አለኝ ፡ የምሰዋው ፡ ከነፍሴ ፡ የሚፈስ የቅኔው ፡ የዜማ ፡ ሽታ ፡ ታጅቦ ፡ በብዙ ፡ ሆታ ከምድር ፡ ይውጣ ፡ ያስተጋባ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ማደሪያ ፡ ይግባ ይገባሃል ፡ እና ፡ ጌታዬ (፬) በስግደት ፡ በአምልኮ ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና ፡ በዕውነት ፡ በመንፈስ ፡ ፊትህ ፡ ልምጣና ፡ ላምልክህ ፡ እንደገና (፫)

Listen on Gubae

Gubae is a free app for Android: mezmur lyrics, the Bible, church events, and a player for the music on your phone.

Get it on Google Play

More songs by Azeb Hailu

See all 66 songs by Azeb Hailu